የወደቁ ጓዶች ሲታወሱ
ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1972 ዓ.ም ድረስ በርካታ የመኢሶን አባላትና ደጋፊዎች በግፍ ተገደሉ። እነዚህን ጓዶች መዘከር ያስፈልጋል በሚል ጽኑ እምነት እኛ ጓዶቻቸው የተገድሉትን ጓዶች ስም ዝርዝር ማጠናቀርና የሕይወት ታሪካቸውን መሰብሰብ ጀመርን።
የስም ዝርዝርና የሕይወት ታሪካቸውን መሰብሰብ ቀላል ስራ አልነበረም። ከጊዜው መርዘም ጋር መረጃ ሊሰጡን የሚችሉ ሰዎች በሕይወት ያለመኖር እንዲሁም በትክክል በጽሁፍ የሰፈረ ታሪክ ለማግኘት ያለመቻላችን ስራችንን በቅልጥፍና ቶሎ ለመጨረስ አላስቻለንም። እንዲያውም ጊዜው በረዘመ ቀጥር የመረጃ ምንጮቻችን እየሳሱ እንደሚመጡ ተረዳን። ስለዚህም በተገኙት መረጃዎች በፍጥነት የተቻለው ያህል ሰርተን ስራችንን ከላጠናቀቅን፣ ልፋታችን መና ሆኖ እንደሚቀር ተገነዘብን።
ስራችንን መልክ ለማስያዝ፣ በቃልና በጽሁፍ ቃለ መጠይቅ አዘጋጀን። የድሮ ጽሁፎችን፣ ሪፖርቶችን ጋዜጦችና መጽሄቶችን አገላበጥን። በአሜሪካ፣ በአውሮፖ እና ኢትዮጵያ የምንገኝ ጓዶች፣ በየጊዜው እየተገናኘን የሰበስብናቸውን መረጃዎች በአንድነት ገምገምን። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አብዮት 50ኛ ዓመት በዓልን እንደ እልባት በመውሰድ አንድ አነስተኛ ጽሁፍ ለማውጣት ወሰንን። ይህም ጥረታችን ተሳክቶ እነሆ “የመኢሶን ሰማዕታት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ የካቲት 1916 ዓ.ም. ለህትመት ሊበቃ ቻለ።
በተጨማሪም ሚያዚያ 6፣ 2016 ዓ.ም በመላው አለም የሚገኙ የሰማእታቱ ቤተሰቦችና ጓዶች በአንድነት ተሰብሰበው ፍቅራቸውንና ክብራቸውን ለሰማዕታቱ ገለጹ።ለአብዛኛዎቹ ለቆሰለ ልባቸው መፅናኛ ፣ የሐዘናቸው መደምድሚያ ሆነላቸው። “የመኢሶን ሰማዕታት” የ130 ጓዶቻችንን ስም ዝርዝርና አጭር የሕይወት ታሪክ ያዘለ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ውስጥ ውስጥ ከሞላ ጎደል የ 112ቱ ሰማዕታት የሕይወት ታሪክ ተዘርዝሯል። በመረጃ እጦት ምክንያት የተቀሩትን 18 ጓዶቻችንን ስም ከመዘርዘር ያለፈ የሕይወት ታሪካቸውን ማስፈር አልቻልንም።
እዚህ መጽሐፍ ላይ የተዘረዘሩት 67ቱ ሰማዕታት ሕይወት ያለፈው በተናጠል ሲሆን 63ቱ የተገደሉት በ11 የቡድን ጭፍጨፋዎች ነው፡፡ እነዚህ ጓዶቻችን 50 ያህሉ የተገደሉት በኢሕአፖ፣ 46ቱ በደርግ፣ 3ቱ እጃቸውን ለደርግ አንሰጥም ብለው የተስው ሲሆኑ የቀሩት የተገደሉት በኦሮሞ ነፃነት እስላማዊ ግንባርና እና የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዲዩ) ነው፡፡ ከሰማዕታቱ 7ቱ ሴቶች ሲሆኑ ከመካከላቸውም 4ቱ ባለ ትዳር እና ከ2 በላይ የልጆች እናቶች ነበሩ። በጊዜው የነበረውን የሴቶችን መለስተኛ የፖለቲካ ተሳትፎ ስናጤን፤ በዚህ ቁጥር የሴት ሰማዕታት መኖር የአላማ ጽናታቸውንና ቆራጥነታቸውን የሚያንጸባርቅ መሆኑን እንረዳለን። እድሜያቸውን ማወቅ ከቻልናቸው ውስጥ አሥራ አራቱቱ ከ30 በታች፣ አሥራ ዘጠኙ ከ30 እስከ 49 ሲሆኑ 3ቱ ብቻ ከ40 በላይ ሆነው እናገኛለን፡፡
የትምህርት ደረጃን በተመለከተ
- ስምንቱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
- አሥሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
- ሃያ አንዱ የዲፖሎማ ተመራቂዎች
- ዘጠኙ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች
- አስራ አራቱ ሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ማለትም MA እና PhD ዲግሪ የሰሩ ነበሩ፡፡
የድርጅቱ ሥም በትክክል እንደሚገልፀው መኢሶን፣ የመላ ኢትዮጵያ ሶሺያሊስት ንቅናቄ ነው፡፡ የመስራቾች፣ የአመራሩ፣ የአባላቱም ምንጭ እንደዚሁ መላ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በዚህ ዝክረ ሰማዕታት መፅሐፍም የሚታየው ይኸው በብዝሕነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ነው፡፡
ከላይ እንደተጠቀስነው ይህ መጽሐፍ በትግሉ ወቅት ሕይወታቸው ያለፈውን ሁሉ በተለይም በቀድሞ ሠራዊት ውስጥ በውትድርና ተሰማርተው የተሰዉትን አያካትትም። በውጊያ ላይ ከተሰዉት ሌላ፣ ደርግ የመኢሶን ደጋፊ ወይንም አባላት ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጓዶቻችንን “የቀኝ መንገደኛ” እያለ መረሸኑ የሚዘነጋ አይደለም።
በእዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሳይጠቀሱ የታለፉ ጓዶቻችንን ስምና ታሪክ የመፈለግ ጥረታችን ይቀጥላል።
ይኽ መፅሐፍ፤ ስማቸውና ታሪካቸው በውስጡ ለተዘረዘሩትም ሆነ ለጊዜው በመረጃ እጦት ምክንያት ስማቸው ላልተጠቀሰው ከልባችን ምንጊዜም ሊጠፉ ለማይችሉ ውድ “የመኢሶን ሰማዕታት” ጓዶቻችን የጋራ ማስታወሻ ነው።
———— ************ ———-
የዶ/ር ከበደ መንገሻ፡ አቶ ዳንኤል ታደሰ፡ ምትኩ ተርፋሣ: ደምቢ ዲሣሣ፡ እና ወጣት ዳንኤል (የጄንጅስ ወንድም) አፅም ያረፈበትን ቦታ ለመጎብኘት የተደረገ ጉዞ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ምስክርነት
በግንቦት 1983 ዓ.ም የደርግ መንግሥት በወደቀ ማግስት የዚያን መንግሥት ግፍና ጭፍጨፋ ማጋለጥና ማሳየት እንደ ዋነኛ ጉዳይ ተያዘ። ወደ ሥልጣን የመጣው የኢህአዴግ መንግሥት ተበዳይ ወገኖች ባካሄዱት ቅስቀሳና በወሰዱት እርምጃ አማካይነት ተገፋፍቶ በመፍቀዱ በብዛት ተጨፍጭፈው በጋርዬሺ የይድረስ ይድረስ መቃብር ዓመታት ያስቆጠሩ አፅሞችን በደማቅ የሃዘን ስነስርዓት ማንሳትና የአሟሟታቸውን ሁኔታም ይፋ ማውጣት ተጀመረ። ከነዚህ የደርግ የጭፍጨፋ ቦታዎች አንዱ የልዑል-ራስ አስራተ ካሣ ግቢ በመባል የሚታወቅ ስለነበረ፣ የደርግ የረዥም ጊዜ እስረኞች የነበሩ ሁለት የመኢሶን አባላት የነበሩ ሰዎች በዚያ ግቢ ቁፈራ እየተካሄደ በነበረበት ጊዜ በተለይ በ1971 ከሦስት እስር ቤቶች ተወስደው የተገደሉ ሰዎች አፅም በሚለቀምበት ወቅት፣ በዚያ ቦታ እየተገኙ ባደረጉት ፍለጋ የሁለት ሴት የመኢሶን አመራር አባላት፣ ማለትም የዶ/ር ንግስት አዳነ እና የወ/ሪት ቆንጅት ከበደን አፅሞች ለይተው በማግኘት ለማረጋገጥ ቻሉ። የሁለቱ ጓዶችም አፅም ወላጆቻቸው ወደተቀበሩባቸው ቤተመቃብሮች ተወስደው በክብር አረፉ።
ይህንን ተከትሎ ነበር፣ በነዚሁ ሁለት ጓዶች አነሳሽነት ከጫንጮ ከተማ ምዕራብ ሰኞ ገበያ በሚባለው ስፍራ አካባቢ የወደቁትን የመኢሶን መሪዎችና ዋነኛ አባላት አፅም ያረፈበትን ቦታ ለማግኘትና አውጥቶ በክብር ለማሳረፍ ሙከራ የተጀመረው። የዚህ ሙከራ የመጀመሪያ ክፍል፣ ጓዶቹ የወደቁበትን አካባቢ የሚያሳይ ሰው ማግኘትና በእሱ መሪነት ወደ አካባቢው ሄዶ ትክክለኛ ቦታ አግኝቶ ማረጋገጥ ነበር። ይኸን ለማድረግ ቦታውን የሚያውቀውን ሰው በመያዝ 1ኛ/ የአቶ ዳንኤል ታደሰ ባለቤት ወ/ሮ እንጉዳይ በቀለ 2ኛ/ የቅርብ ጓደኛቸው ወ/ሮ ማንያህልሻል ከበደ 3ኛ/ ፕ/ር ካሣሁን ብርሃኑ 4ኛ/ ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ እና 5ኛ/ አቶ ግርማ አለማየሁ በአንድ ላይ ሆነው ወደ አካባቢው አመሩ። በአካባቢው ደርሰው መጠያየቅ እንደጀመሩ ወዲያውኑ የአካባቢው ሰዎች ቀርበዋቸው የመጡበትን ጉዳይ ምንነት ካዳመጡ በኋላ አንዱ ሽማግሌ የሚከተለውን አሏቸው።
“እኛ የሟቾቹን ማንነት፣ ለምን ወደዚህ መጥተው እንደተሰዉ እናዉቃለን። የተቀበሩበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን የአቀባበራቸውንም ሁኔታ እናውቃለን። ምክንያቱም እኛ ራሳችን ነን የቀበርናቸው። ነገሩ እንደዚህ ነው። በነሐሴ ወር መጨረሻ እሁድ ዕለት ከዚህ ማዶ ያለ ቦታ ላይ የደርግ ወታደሮች ደርሰውባቸው ተገደሉ። ከዚያም ወታደሮቹ አስክሬናቸውን ከገደሉበት ቦታ አምጥተው ልብሳቸውን ገፈው እዚሁ ገበያችን አጠገብ ጣሏቸው። በሚቀጥለው ቀን ሰኞ ዕለት ገበያችን የሚውልበት ቀን እንደመሆኑ፣ ሕዝብ አስክሬናቸውን ያይ ዘንድ እንዳይነሳ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፈው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ሰኞ ጠዋት ሕዝቡ ወደ ገበያ መጉረፍ ሲጀምር፣ የሚያውቃቸው ሰዎች አስክሬን ጭምር እንደዚያ መውደቁን እያየ በመደንገጥ እየሸሸ ይመለስ ጀመር። የዚያን ቀን ገበያው ሳይቆም ቀረ። ወደ ማምሻው ላይ በአካባቢው የምንኖር ሰዎች፣ ለቀበሌው መሪዎች “እንዴት እንዲህ ይደረጋል? ለሰውስ ክብር ሆነ ለመጠጥ ውሃው ሲባል አፈር መልበስ የለባቸውም ወይ?” ብለን በመለመን እሺ አሰኘናቸው። ከየቤታችንም ቡቱቶ ፈላልገንና የዛፍ ልጥ እና ቅጠል ጎዝጉዘን በቆፈርነው የጋራ መቃብር አምስቱንም ሟቾች ቀበርናቸው። የሚገርመኝ ያ መልከ-መልካሙ ሚኒስትር (ዳንኤል ታደሠ) ከሞተ ከ24 ሰዓት በኋላም በሕይወት ያለ ይመስል ነበር። ከታች ዶክተሩን (ከበደ መንገሻን) ከዚያ ሚኒስትሩን፣ ቀጥሎ ደምቢ (ዲሣሣን) እና ምትኩ (ተርፋሳን) በመጨረሻም ስሙን የማናውቀውን ወጣት (ዳንኤል፤ የጄንጅስን ወንድም) አድርገን ቀበርናቸው። ከዚያም ለምልክት እና ለማስታወሻ ብለን እነዚህን እንደዚህ አድገው የምታዩዋቸውን ባህርዛፎች በክቦሺ ተከልን ። እኛ እዚህ መጥታችሁ ስላየናችሁ ደስ ብሎናል። ሌላው የደርግ ሰለባ ከየቦታው አፅሙ ሲነሳ የእነኝህ ወድቆ መቅረቱ ለምንድነው? ወገን የላቸውም ወይ? ስንል ነበር። አሁንም፣ ምንም ቢዘገይ መምጣታችሁ መልካም ነው።”
አረጋዊው ይህን ብለው እንደጨረሱ ከመካከላቸው ያሉ ሰዎች “እንዲያውም ይኸውና ሟቾቹ በመጨረሻዋ ቀናቸው አርፈውበት የነበረው ቤት ባለቤት፤ አሁን በአጋጣሚ ዘመድ ጥየቃ መጥቶ ከነበረበት ጠርተነው መጥትዋል። እሱ የመጨረሻቸውን ታሪክ በትክክል ይንገራችሁ፣ አዳምጡት” ብለው አንድ ሌላ አረጋዊ ሰውን አቀረቡ። ሰውዬውም ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የሚቀጥለውን የምስክርነት ቃል ሰጡ። “እሁድ ጠዋት (ነሐሴ 3ዐ ቀን 1969) አምስቱ ሰዎች እኔ ቤት ደረሱ፣ እዚያው አርፍደው ከሰዓት በኋላ ላይ ወታደሮች ቤቱን እንደከበቡት ተረዳንና፣ ወዲያውኑ ዶክተሩና ሚኒስትሩ (ዶ/ር ከበደ መንገሻ እና አቶ ዳንኤል ታደሰ)፣ ሦስቱን ወጣቶች “እናንተ የአመራር አባላት ስላልሆናችሁ እጃችሁን ስጡና ሕይወታችሁ ይትረፍ ውጡ” አሏቸው። ከዚያም ሁለቱ “ደህና ሁን፣ ደህና ሁን” ተባብለው ሽጉጦቻቸውን ሲያነሱ፣ እኔ ደግሞ “ምነው ጌቶቼ እንዴት ራሳችሁን ታጠፋላችሁ”፣ እያልኩ ስለምናቸው፣ ሁለቱም በየሽጉጦቻቸው ጭንቅላቶቻቸውን መትተው ወደቁ። ይህ እየሆነ ሳለ ሦስቱ ወጣቶች ደግሞ እየተኮሱ ወጥተው ከባድ መትረየሶች ጠምደው ይጠብቋቸው በነበሩት ወታደሮች የጥይት እሮምታ እየተመቱ ወደቁ። ወታደሮቹ የሁሉንም አስከሬን በገበሬ አሸክመው ወደ ሰኞ ገበያ በማምጣት በዚህ ጣሏቸው።”
ከአዲስ አበባ ቦታውን በማጣራት የሄዱት ጓዶች ይህንን እንደሰሙ፣ ወዲያው በቅርብ ወደሚገኘው ጓዶቹ ወደተቀበሩበት ቦታ ከአካባቢው ሰዎች ጋር አመሩ። የአካባቢው ሕዝብም ከየአቅጣጫው እየመጣ ቁጥሩ ጨመረ። በተቀበሩበት ቦታ በክቦሺ የተተከሉት እና 12 ዓመታት ያስቆጠሩት የባህርዛፎችም እጅግ አድገው ቦታውን ልዩ ግርማ አሳድረውበት ነበር። የአካባቢው ነዋሪ ወንዶችና ሴቶችም የእንግዶቹን ማንነት ሲያውቁ እንደ አዲስ በእንባ መራጨት ጀመሩ። የአቶ ዳንኤል ታደሰ ባለቤት ወ/ሮ እንጉዳይም በመቃብራቸው ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀመጠች። ከዚያ ጉዞ መልስ ጓዶች አፅማቸውን ከዚያ አውጥቶ በመካነ-መቃብር ለማሳረፍ ለወረዳው አስተዳደር ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ከበላይ መልስ ስለልተሰጠበት ምንም ማድረግ አይቻልም ተባሉ። ምናልባትም እነኝህ አምስት ገዶች ሙያ ሰርተው በወደቁበት መሬትና አረንጓዴ ሃውልት ባስቀመጠላቸው ሕዝብ የመኖሪያ ቦታ መቅረታቸው፣ ያምኑበት የነበረው ዓለምአቀፋዊነት፣ ያምኑበት የነበረው መላ ዓለም የሁሉም የሰው ልጆች ቤት መሆን ምስክር ሆኖ ይቀጥል ዘንድ የታሪክ መልካም ፈቃድ ሁን ያለው መደምደሚያ ይኸኛው ይሆናልና፤ ይሁን!
(የእነ ዶ/ር ከበደ መንገሻን አጽም ለመፈለግ ከሄዱት ጓዶች አንዱ)
በጎንድር ክ/ሃገር በመኢ ሶን አባላት ፤ካድሬዎችና ደጋፊዎች ላይ በተደረገው ጭፍጨፋ የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር
በክፍ ለሃገሩ በመኢሶን ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከሌሎች ክ/ሃገራት ለየት ባለና በከፋ መልክ ነበር። አብዛኛው ግድያ በቀጥታ በደርግና በኢህ አፓ የተፈጸመ ቢሆንም ኢህአፓ በደርግና በህዝብ ድርጅት ይባል በነበረው ሰርጎ በመግባት ግድያ የተካሄደ ሲሆን ኢዲዩ እና ቲፒኤሌፍ የተባሉትም የበኩላቸውን አሰቃቂ ግድያ አከናውነዋል። ለግንዛቤ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፤ በጎንደር ክ/ሃገር የድርግ አባል የነበረውና በጭካኔው ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሻለቃ መላኩ ተፈራ ይመራው የነበረው በፊት መንጥር በኋላ ደግሞ መብረቅ የሚባል ወታደራዊ የጦር ፍ/ቤት ነበረው። በዚህ ኮሚቴ ተሳታፊ የነበሩት ህዝብ ድርጅት ጽ/ቤት ፤ የጎንደር ከተማ ከንቲባና ምክትሉ ፤የክ/ሃገሩ ፖሊስ ተወካይና ከጦሩ አንድ ተወካይ ይሳተፉ እንደበበር ምስጢር አልነበረም።
የዚህ የቀይ ሽብር ኮሚቴ የራሱ የምርመራ ቡድንና ቀይ ሽብሩን የሚፈጽሙ ምርጥ ቅልብ ስፔሽያሊስቶች ነበሩት። የቡድኑ ሰብሳቢ መነላኩ ተፈራ ቢሆንም ኢህአፓ ደግሞ በራሱ ፍርድ ፊት ለፊት ከሚገድለው በተጨማሪ በጣም በረቀቀና በሚስጢር ሰርጎ በመግባት በኮሚቴው ውስጥ ቢያንስ ሁለት አባላት ነበሩት።
…..በ1970 መጨረሻ በደርግ መፈክር” ደም ስጡ ደም እንስጥ” በሚለው መፈክር መሰረት በአረመኔው መላኩ ተፈራ በሚመራው መብረቅ በተሰኘው ኮሚቴ ውሳኔ መሰረት እጅ እግራቸውና መላ ሰውነታቸው በቶርች ወንበር ተጠርፎ እየታሰረ በጤና ጥበቃ ሰራተኞች ደማቸው ተሟጦ ከተወሰደ በኋላ በጀምላ አዘዞ ከተማ በሚገኘው የጀምላ የቀይ ሽብር መቃብር ተቀብረዋል። አንዲት ወጣት የመኢሶን ካድሬ ጓደኛ ነች ተብላ በመጠርጠሯ ብቻ በኢህአፓ ጓደኞቿ የይስሙላ ፓርቲ ተጠርታ ከሄደች በኋላ በኢህአፓ ውሳኔ በገመድ ተንጠልጥላ ተገድላለች።
…..በጎንደር ክ/ሃገር ደንቀዝ በሚባል ቦታ እጅግ ዝነኛ፤ ታዋቂና የተከበረ ገበሬ የነበር፣ የእህቱ ልጅ የመኢሶን ካድሬ በመሆኑ ምክንያት ህዝብን በመንግስት ላይ ሊያነሳሳ ይችላል ተብሎ በመኢሶን ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ህዳር 1970 ከሌሎች አራት ገበሬዎች ጋር ጎንደር ከተማ አካባቢ ከምትገኘው ጠዳ ከተማ ላይ ለገብያ የመጣው ህዝብ እያየ በመላኩ ገዳይ ቡድን በጠራራ ጸሃይ በጥይት ተጨፍጭፈው ሬሳቸው ሳይነሳ እንዲውል ተደርጓል።
(ጎንደር የነበረ የመኢሶን አባል ምስክርነት)
ሰላም የተከበራችሁ የመኢሶን ቤተሰቦች !
ከዛሬ 50 አመት በፊት በሃገራችን የሆነውን የየካቲቱን ሥር ነቀል አብዮት በማስታወስ ከዚሁ ታሪክ ጋር የተሳሰረውን የመኢሶን ሰማእታት በማሰብም መዘከሩ ፍጹም ተገቢና ትክክል ስራ ነው። አስባችሁ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ይህንን የሰማታት መጽህፍ አዘጋጅታችሁ ከማበርከታችሁም አልፎ ይህንን እለት ለመዘከር እንድንሰባሰብ በማድረጋችሁ አዘጋጆቹ ጓዶቻችን ፍጹም የከበረ ምስጋና ይድረሳችሁ ።
ለየካቲቱ አብዮት መከሰት ከአብዮቱ በፊት የነበረ ችግሮች ሚና እንደነበራቸው ይታወሳል። የፍትህ እጦት፣ የአስተዳደር በደል፣ ርሃብ፣ የመሳሰሉት ችግሮች ሁሉ ተደማምሮ ሚሊዮን አርሶ አደሮችን፣ ሠራተኛውን፣ ተማሪውን፣ ሠራዊቱን፣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችንና እንዲሁም በከተማ ታክሲ ነጂዎችን፣ አስተማሪዎችን ሁሉ አነቃንቆ ብሶታቸውን አንግበው በመነሳት ያመጡት የለውጥ ማእበል ነው። ይህም የየካቲቱ አብዮት ይባላል። ይህንን ሁሉ የምታውቁትን ሃተታ መዘርዘሬ በተሳሳተ ትረካ ዛሬ ይህንን ሃቅ ክደውና ቀጥፈው የዚያን ጊዜ ትውልድ አሲሮ ያመጣው ክስተት ሲሉ ስለምሰማ ነው። የየካቲቱን አብዮት ያ ትውልድ አልፈጠረውም። አልመራውም፣ የመንግስት ሥልጣን ጨብጦም አላስተዳደረውም። የ66ቱ አብዮት ዛሬ ጊዜው ርቆ ደብዘዝ ብሎ ደምቆ ባይታይም አለም ላይ ከተካሄዱ ጥቂት አብዮቶች የሚመደብ እንደሆነ በሰፊው የተነገረለት ነው። እጅግ ሥር ነቀል ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ የነበረውን ስርአት አድሶ አዲስ ስርአት የማዋቀር አላማም ይዞ እንደነበርም ይታወሳል። የየካቲቱ አብዮት ኢትዮጵያዊያን በጋራ ያመጡት ድል ነው። ታላቅ የሆነ የታሪክ ምእራፍ ነው።
የየካቲቱ አብዮት በፈጠረው ክስተት ተያይዞ ዛሬ የምንዘከረው የዚያ ትውልድ አስተዋጾም በተለይም ለውጡ ግቡን እንዲመታ የአደረገው ትግል ሊነገርም፣ ሊወደስም ይገባዋል። የሃገራቸውን ኋላቀርነት ተቆጭተው ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነበት፣ ዲሞክራሲ ሥርአት ለማነጽ ቃልኪዳናቸውን አክብረው እነዚህ የመኢሶን ሰማእታት ለብሩህ ራእይ፣ ህልማቸው በመታገል ህይወታቸውን ለግሰዋል። ለተበደሉና ፍትህ ላጡ ወገኖች በጽናት ቆመው አልፈዋል። ይህ ታሪካቸው በኢትዮጵያ ብርሃን ሲያይ ደምቆ እንደሚቀር አያጠራጥርም። እኛም ዛሬ ስንዘክራቸው፣ ዛሬም ያልረሳናቸው በውስጣችን ያሉ መሆኑ በሚገባ ሊታወቅ ይገባል። አንዳንዶቻችሁም እዚህ ዛሬ የታደማችሁ ከእስር ቤት ከጒናችሁ አጣድፈው ለግድያ ሲወስዷቸው ለመጨረሻ በአይናቸው ሰርቀው ተሰናብተዋችሁ ሲለያችሁ መቼ ይሆን ቀጣዩ ተራዬ ብላችሁ የተረፋችሁ ያ የጨለማና የሰቀቀን ገጽታ፣ ዛሬም እንደሚታወሳችሁ፤ አልፎ ተርፎም ቀሪ መስካሪም ናችሁ። እነዚህ የመኢሶን ሰማእታት የታገሉለት አላማ ተደናቅፎና ግብ መቶ ባይሳካም በአደረጉት የአጭር ጊዜ ተጋድሎ በቀላሉ የማይገመት ውጤቶችም አስገኝተው አልፈዋል። የታገሉለት አላማ ጭሰኝነት፣ ገባርነትን አላቋል። የሃይማኖት ፣ የብሄር እኩልነት እንዲታወቅ በር ከፍቷል። የፊውዳሉን የዘውድ አገዛዝ ሥርአት አፍርሷል።
የየካቲቱን የታሪክ ምእራፍ ማክበር ሲታሰብ በቅርቡ በተዛባ ትርካት በቦታው ያልነበሩ አስመሳዮች በደፈናው ምንም እንኳን ግራጫ ገጽታ እንዳለው ቢታውቅም በማጉደፍ ስለው ሲዘምቱ መስማትም ችለናል። ያ! ትውልድ ያ! ዘመን እየተባለ በተዛባ አነጋገር የሚሰጠው ትርካት በማስተካከል ሃቅን ማስተላለፍ ይገባል። መጭው ትውልድ የትላንቱን በውል አውቆ ከዚያም ተምሮ ወደ ተሻለ ለመሻገር እነዚህ የመኢሶን ሰማእታት የተጓዙበት ታሪክ ሂደት በስፋትም ፣በጥልቀትም ለማውቅ ይህ መጽሃፍ አይነተኛ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል። ወደፊትም ስለ ሰማእታቱ ብዙ ያልተነገሩ በየጓዳችን ያሉ ታሪኮች፣ ሰነዶች ተልቃቅሞ በቀጣይ እትምት የሚታከሉበት መላ መፍጠሩ ይታሰብበት በሚል በዚህ አጋጣሚ ሃሳቤን አቀርባለሁ።
Remembering My Dad Daniel Tadesse
As Daniel Tadesse’s child, I’ve often wondered about the legacy my father left behind. I think it’s fair to say that it’s a precious legacy, made up of stories of heroic deeds, courage and sacrifice, but also a psychological legacy that has deeply affected our family. For me, this legacy has many facets, from inspiration and pride to emotional challenges and profound questions of values and worldview. The example of determination and courage set by Daniel Tadesse and other members of my family is a source of pride and inspiration for me. I can say that integrity and sincerity of commitment are examples that I was given to follow very early in my childhood.
I have also inherited a deep trauma and complex grief given the circumstances in which Daniel Tadesse and other members of my family died, as well as the difficult conditions my mother Engudai Bekele had to face in our childhood. This situation was exacerbated by the fact that the expression of sadness and pain was itself restrained. The way my family members faced adversity, following the disappearances of my father Daniel Tadesse, my uncle Desta Tadesse and my aunt Dr Nigist Adane and their comrades, has always been very dignified and is also part of my heritage. Early on, I felt the need to live up to my family history, to perpetuate the legacy and to live by the examples I was given to see.
I thank my mother Engudai Bekele, my grandparents W/ro Fantaye Ruphael and Fitawrari Tadesse Markos and my aunt Zenebework Tadesse for being the guardians of my father’s memory. As Victor Hugo said, “Remembrance is the invisible presence”. They brought Daniel Tadesse’s memory to life in our children’s eyes and gave us a unique legacy. I would also like to thank those responsible for this memorial project. The publication of this book will enable us to pay a well-deserved tribute to people who demonstrated courageous acts and sacrifices for ideals they felt were right. The losses were considerable, and our duty is to remember and pass on to future generations. Passing on to help preserve peace and justice, while contributing to the prevention of past mistakes. Pass it on as a commitment to a better future, where the lessons of the past are used to guide present and future actions.
In Memory of My Beloved Father
My dad, Terefe Woldetsadik, was born in Woliso, Shewa province. He completed his early elementary education in Woliso while living with his single mom and four siblings (two brothers and two sisters). He was the third child. He moved to Addis Ababa at an early age to continue his education and attended Ameha Desta, where he completed high school. I was told that my dad was highly regarded at Ameha Desta, and both he and Gash Lemma Argaw served on the student council as president and secretary, respectively, until they completed high school. After graduating, both continued their higher education at Addis Ababa University (AAU).
My mom, Atnaf-Alem Yemam, attended Woizero Sehin School in Dessie, Wello province, where she completed her elementary education. She then moved to Addis Ababa and joined Etege Menen boarding school, where she completed high school. My parents met at AAU and graduated together in 1964. They got married while my dad was still working at AAU as a student public relations director for one year. Their wedding ceremony took place at the AAU’s student hall, according to Auntie Aslaku and both my late uncles. The wedding was expedited because my dad had received a scholarship from ISS University in the Netherlands and decided to take my mom along with him.
The one thing I loved most about my parents, and have always been proud of, especially about my dad, is that besides his strength in the academic world, he genuinely loved and cared for people who were less fortunate.For instance, although I was told about many of my dad’s great qualities, the story that resonates with me the most is that he used to give the people who worked in our household as a security guard and maid the opportunity to attend night school. He even let our security guard, Mulugeta, work at the የካቲት 66 የፖለቲካ ትምህርት ቤት (Yekatit 66 Political School) during the day while living with us and performing his duties as a security guard at night alongside my uncles at our ባምቢስ home, where we were living at the time. I think this fact deserves to be mentioned in my own writing if I find the strength to do that!
Years later, after both my parents were assassinated by the Derg, both Mulugeta and our former home helper, who became Mulugeta’s wife, came to Auntie Aslaku’s home to visit me and shared their personal testimonies about what kind of people my late parents were.
In Memory of My Beloved Mother
Atnaf-Alem Yemame was born on November 21, 1945 G.C. (Hedar 18, 1938 Eth.C.) in Dessie, Wollo, Ethiopia. She began her early education in Dessie at the Empress Menene Elementary School, where she completed her elementary education in 1951 Eth.C. She then moved to Addis Ababa to further her education at the Empress Menen Secondary School, graduating in 1954 Eth.C. From 1955 to 1959 Eth.C., she continued her higher education at Haile Selassie I University in Addis Ababa, where she received her diploma from the School of Social Work. It was during her time at Haile Selassie I University that she met her college sweetheart, my dad, Dr. Terrefe Woldetsadik (one of the founders of the All Ethiopian Socialist Movement [Meison]), whom she married in the early 1960s Eth.C.
In August 1968 G.C., my mom and dad both went to The Hague, Netherlands, to continue their higher education at the Institute of Social Studies (ISS). My mom received her degree in Urban Social Development on June 29, 1973, followed by her master’s degree in social science on September 4, 1974. My mom is survived by her two children: me, Gashu Terrefe Woldetsadik (born on August 10, 1970 G.C. in The Hague, Netherlands), and Tekalegn Terrefe Woldetsadik (born on February 28, 1977 G.C. in Addis Ababa and deceased on August 7, 2003 G.C.). May he rest in peace and rise in glory.
My mom was murdered by the Derg regime’s hit squad alongside my dad in December 1978 G.C. (early Tahesas 1970s Eth.C.), leaving behind her two children (7 years old and 5 months old at the time). Currently, the only survivor of the Terrefe family is me, Gashu Terrefe, who has lived in the United States of America since November 26, 1990 G.C., in Maryland State with my wife. Both my dad and mom would have been grandparents to three children: my two children, Matthewos Gashu Terrefe, 20, and Yonathan Gashu Terrefe, 18, as well as my brother Tekalegn’s son, Matthew Tekalegn Terrefe, 22, who lives in Addis Ababa.
My mom was a brave and patriotic Ethiopian woman who sacrificed her life fighting for a great cause alongside her beloved husband, Dr. Terrefe, my dad, and nine other fellow MEISON active members near Ambo town, in west-central Ethiopia, in December 1978 Eth.C. She is always remembered by her children and her siblings as a courageous mother who loved her country and for her altruism and devotion as a social worker to always help those members of our society who were in dire need.
May both my parents rest in peace.
ዶ/ር ንግስት አዳነ
ዶር ንግስት አዳነ በጣም የምወዳትና የማከብራት ጓደኛዬ ናት። ከሩቁ ስትታይ ገፅታዋ የሚያስፈራ ቢመስልም ሲቀርቧት ግን በጣም ተግባቢ ቀልደኛና ደግ ሰው ነች። በተጨማሪም ትጉህ ሰራተኛ ብልህ መፅሀፍ አንባቢና ከባድ የሆኑ አስተሳሰቦችን በቀላል ቃላት የምታስረዳ ለአመነችበት ከልቧ የምትሰራ ቆሬጥ ጠንካራ ጓድ ነበረች ። የመኢሶን የሴቶች ድርጅት በተመሰረተበት ስብሰባ ላይ በመሪነት፣ በአስተማሪነትና የሁሉንም ሃሳብ በማዳመጥ በተነሱት ሃሳቦች ላይ ስምምምንት ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት ታደርግ ነበር።
ምን ያህል ቆራጥ እንደሆነች አንድ ምሳሌ ልስጥ –
ከርቸሌ በነበርንበት ጊዜ በየአመቱ ምዝገባ ይደረግ ነበር ።ስም እድሜ ከተሞላ በኋላ “የታሰርሽበትን ስራ የሰራሽው አውቀሽ ነው ወይስ ተወናብደሽ ነው” የሚል ጥያቄ ይቀርባል። እኔ እስከማውቀው ድረስ ከንግስት በስተቀር “አውቄ ነው“ ብሎ የሚመልስ ማንም የለም። ነገር ያከብዱባታል ብየ ስለምፈራ አንድ ቀን “ንግስት ምን ቸገረሽ ተወናብጀ ነው” በያቸው አልኳት። እሷም “ከዚያስ ማን አወናበደኝ ልበል” አለችኝ ።ሌላ ደግሞ ለልጇ ለሀዲስ የነበራትን ፍቅርና ናፍቆት አስታውሳለሁ። አንድ ጊዜ ለልደቱ የሳንቲም መያዣ ቦርሳ ለመስራት የማታውቅበትን ዳንቴል መስራት እንደምንም ተለማምዳ ሰርታ ስትጨርስ የተሰማት ደስታ አይረሳኝም። በእስር ቤት በነበረችበት ጊዜ ምግብ አብረን ስንመገብ አዘጋጅና አቅራቢ በተራ ነበር ። ንግሥት ተረኛ በሆነችበት ቀን በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ሌሎቻችን በተራችን የመጣውን ምግብ አሙቆ ከማቅረብ የበለጠ አናደርግም። በሷ ተራ ጊዜ ግን የምንጠቀምባቸው እቃዎች በሙሉ እስኪያብረቀርቡ ታጥበው ሁሉ ዕቃ ተስተካክሎ ይቀመጣል ።
ንግስት ትልቅ ሰው ነች ባህሪዋ ፣ እኔ የሰውን ባህሪ የምመዝንበት መለኪያ ሆናኛለች።
(ከእስር ቤት ጓዶቿ አንዷ)
ዶ/ር ንግስት አዳነ
ዶ/ር ንግሥት አዳነን በደንብ ያወቅህዋት ከርቸሌ አስር ቤት በነበርንበት ጊዜ ነበር:: ዶ/ር ንግስት በኔ አመለካከት ቁጥብ ያለች: ጊዜዋን በቁም ነገር የምታሳልፍ: ፅድትና ጥንቅቅ ያለች ነበረች:: ለመቅረብ ብዙ የማትከብድ ብትሆንም በጣም አከብራትና እፈራትም ስለነበር አየወደድኳት የምፈልገውን ያህል ሳልቀርባት ቀረሁ:: ብዙ የማታሳየው ቢሆንም ሩህሩህና አዛኝ ሰው ትመስለኝ ነበር:: በትእግሥቷ: በቀና አመለካከቷና በአውነተኝነቷ ሁሌም ስለአብዮት ባስታወስኩ ጊዜ ሁሉ ከማስታውሳቸው ውስጥ የመጀመሪያው ረድፍ ውስጥ የማገኛት: በጣም የምወዳት: የማከብራትና የማደንቃት ታላቅ ኢትዮ ጵያዊት ነበረች::
(ከእስር ቤት ጓዶቿ አንዷ)
In Memory of my Beloved Brother
Yohannes Mesfin, born in Addis Ababa, Ethiopia, in June 1952, spent his formative years in the bustling city he called home. He commenced his education at St. Joseph School, a private Catholic institution, and excelled academically until the 11th grade when his unwavering commitment to revolutionary leadership and social justice led to his permanent expulsion.
Coming from an affluent background, Yohannes always championed the rights of the less fortunate, the exploited, and marginalized members of society. Even in his youth, he displayed remarkable scholarly prowess, consistently ranking at the top of his class. An avid reader and incredibly disciplined, he also possessed an exceptional aptitude for understanding global politics and the political positions of various countries.
As a teenager, Yohannes contributed thought-provoking articles on political issues to the Ethiopian Herald, earning 25.00 birr per article in the late 1960s. His early exposure to the writings of Marx and Lenin fueled his passion for political discourse, often leading to spirited discussions at the family dinner table with his supportive father, Mesfin Zellelow, who encouraged Yohannes to express his own views freely.
During his high school years, Yohannes organized and led demonstrations, rallying students to stand in solidarity with political movements seeking to reform the prevailing monarchy’s business practices. His activism eventually led to his permanent expulsion from St. Joseph School, along with a handful of like-minded peers. Yohannes’s politically rebellious behavior resulted in a six-month prison sentence, which his father promptly resolved by paying the fine. Fearing potential repercussions from the emperor, Yohannes’s father made the pivotal decision to send him to the United States to complete his high school education.
Yohannes successfully completed high school at Oak Grove High School, in Fargo, North Dakota, and embarked on his college journey at Concordia College. However, soon after, he set his sights on moving to Berlin to complete his educational pursuits.
Beyond his academic and political endeavors, Yohannes was a loving brother to three boys and a girl at the time. Known for his kindness, compassion, unwavering integrity, and deep commitment to his beliefs, Yohannes Mesfin stood as a shining example of an individual dedicated to making the world a better place through knowledge and social justice.
ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1972 ዓ.ም ድረስ በርካታ የመኢሶን አባላትና ደጋፊዎች በግፍ ተገደሉ። እነዚህን ጓዶች መዘከር ያስፈልጋል በሚል ጽኑ እምነት እኛ ጓዶቻቸው የተገድሉትን ጓዶች ስም ዝርዝር ማጠናቀርና የሕይወት ታሪካቸውን መሰብሰብ ጀመርን።
የስም ዝርዝርና የሕይወት ታሪካቸውን መሰብሰብ ቀላል ስራ አልነበረም። ከጊዜው መርዘም ጋር መረጃ ሊሰጡን የሚችሉ ሰዎች በሕይወት ያለመኖር እንዲሁም በትክክል በጽሁፍ የሰፈረ ታሪክ ለማግኘት ያለመቻላችን ስራችንን በቅልጥፍና ቶሎ ለመጨረስ አላስቻለንም። እንዲያውም ጊዜው በረዘመ ቀጥር የመረጃ ምንጮቻችን እየሳሱ እንደሚመጡ ተረዳን። ስለዚህም በተገኙት መረጃዎች በፍጥነት የተቻለው ያህል ሰርተን ስራችንን ከላጠናቀቅን፣ ልፋታችን መና ሆኖ እንደሚቀር ተገነዘብን።
ስራችንን መልክ ለማስያዝ፣ በቃልና በጽሁፍ ቃለ መጠይቅ አዘጋጀን። የድሮ ጽሁፎችን፣ ሪፖርቶችን ጋዜጦችና መጽሄቶችን አገላበጥን። በአሜሪካ፣ በአውሮፖ እና ኢትዮጵያ የምንገኝ ጓዶች፣ በየጊዜው እየተገናኘን የሰበስብናቸውን መረጃዎች በአንድነት ገምገምን። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አብዮት 50ኛ ዓመት በዓልን እንደ እልባት በመውሰድ አንድ አነስተኛ ጽሁፍ ለማውጣት ወሰንን። ይህም ጥረታችን ተሳክቶ እነሆ “የመኢሶን ሰማዕታት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ የካቲት 1916 ዓ.ም. ለህትመት ሊበቃ ቻለ።
በተጨማሪም ሚያዚያ 6፣ 2016 ዓ.ም በመላው አለም የሚገኙ የሰማእታቱ ቤተሰቦችና ጓዶች በአንድነት ተሰብሰበው ፍቅራቸውንና ክብራቸውን ለሰማዕታቱ ገለጹ።ለአብዛኛዎቹ ለቆሰለ ልባቸው መፅናኛ ፣ የሐዘናቸው መደምድሚያ ሆነላቸው።
“የመኢሶን ሰማዕታት” የ130 ጓዶቻችንን ስም ዝርዝርና አጭር የሕይወት ታሪክ ያዘለ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ውስጥ ውስጥ ከሞላ ጎደል የ 112ቱ ሰማዕታት የሕይወት ታሪክ ተዘርዝሯል። በመረጃ እጦት ምክንያት የተቀሩትን 18 ጓዶቻችንን ስም ከመዘርዘር ያለፈ የሕይወት ታሪካቸውን ማስፈር አልቻልንም።
እዚህ መጽሐፍ ላይ የተዘረዘሩት 67ቱ ሰማዕታት ሕይወት ያለፈው በተናጠል ሲሆን 63ቱ የተገደሉት በ11 የቡድን ጭፍጨፋዎች ነው፡፡ እነዚህ ጓዶቻችን 50 ያህሉ የተገደሉት በኢሕአፖ፣ 46ቱ በደርግ፣ 3ቱ እጃቸውን ለደርግ አንሰጥም ብለው የተስው ሲሆኑ የቀሩት የተገደሉት በኦሮሞ ነፃነት እስላማዊ ግንባርና እና የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዲዩ) ነው፡፡
ከሰማዕታቱ 7ቱ ሴቶች ሲሆኑ ከመካከላቸውም 4ቱ ባለ ትዳር እና ከ2 በላይ የልጆች እናቶች ነበሩ። በጊዜው የነበረውን የሴቶችን መለስተኛ የፖለቲካ ተሳትፎ ስናጤን፤ በዚህ ቁጥር የሴት ሰማዕታት መኖር የአላማ ጽናታቸውንና ቆራጥነታቸውን የሚያንጸባርቅ መሆኑን እንረዳለን።
እድሜያቸውን ማወቅ ከቻልናቸው ውስጥ አሥራ አራቱቱ ከ30 በታች፣ አሥራ ዘጠኙ ከ30 እስከ 49 ሲሆኑ 3ቱ ብቻ ከ40 በላይ ሆነው እናገኛለን፡፡
የትምህርት ደረጃን በተመለከተ
- ስምንቱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
- አሥሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
- ሃያ አንዱ የዲፖሎማ ተመራቂዎች
- ዘጠኙ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች
- አስራ አራቱ ሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ማለትም MA እና PhD ዲግሪ የሰሩ ነበሩ፡፡
የድርጅቱ ሥም በትክክል እንደሚገልፀው መኢሶን፣ የመላ ኢትዮጵያ ሶሺያሊስት ንቅናቄ ነው፡፡ የመስራቾች፣ የአመራሩ፣ የአባላቱም ምንጭ እንደዚሁ መላ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በዚህ ዝክረ ሰማዕታት መፅሐፍም የሚታየው ይኸው በብዝሕነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ነው፡፡
ከላይ እንደተጠቀስነው ይህ መጽሐፍ በትግሉ ወቅት ሕይወታቸው ያለፈውን ሁሉ በተለይም በቀድሞ ሠራዊት ውስጥ በውትድርና ተሰማርተው የተሰዉትን አያካትትም። በውጊያ ላይ ከተሰዉት ሌላ፣ ደርግ የመኢሶን ደጋፊ ወይንም አባላት ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጓዶቻችንን “የቀኝ መንገደኛ” እያለ መረሸኑ የሚዘነጋ አይደለም።
በእዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሳይጠቀሱ የታለፉ ጓዶቻችንን ስምና ታሪክ የመፈለግ ጥረታችን ይቀጥላል።
ይኽ መፅሐፍ፤ ስማቸውና ታሪካቸው በውስጡ ለተዘረዘሩትም ሆነ ለጊዜው በመረጃ እጦት ምክንያት ስማቸው ላልተጠቀሰው ከልባችን ምንጊዜም ሊጠፉ ለማይችሉ ውድ “የመኢሶን ሰማዕታት” ጓዶቻችን የጋራ ማስታወሻ ነው።
———— ************ ———-
የዶ/ር ከበደ መንገሻ፡ አቶ ዳንኤል ታደሰ፡ ምትኩ ተርፋሣ: ደምቢ ዲሣሣ፡ እና ወጣት ዳንኤል (የጄንጅስ ወንድም) አፅም ያረፈበትን ቦታ ለመጎብኘት የተደረገ ጉዞ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ምስክርነት
በግንቦት 1983 ዓ.ም የደርግ መንግሥት በወደቀ ማግስት የዚያን መንግሥት ግፍና ጭፍጨፋ ማጋለጥና ማሳየት እንደ ዋነኛ ጉዳይ ተያዘ። ወደ ሥልጣን የመጣው የኢህአዴግ መንግሥት ተበዳይ ወገኖች ባካሄዱት ቅስቀሳና በወሰዱት እርምጃ አማካይነት ተገፋፍቶ በመፍቀዱ በብዛት ተጨፍጭፈው በጋርዬሺ የይድረስ ይድረስ መቃብር ዓመታት ያስቆጠሩ አፅሞችን በደማቅ የሃዘን ስነስርዓት ማንሳትና የአሟሟታቸውን ሁኔታም ይፋ ማውጣት ተጀመረ። ከነዚህ የደርግ የጭፍጨፋ ቦታዎች አንዱ የልዑል-ራስ አስራተ ካሣ ግቢ በመባል የሚታወቅ ስለነበረ፣ የደርግ የረዥም ጊዜ እስረኞች የነበሩ ሁለት የመኢሶን አባላት የነበሩ ሰዎች በዚያ ግቢ ቁፈራ እየተካሄደ በነበረበት ጊዜ በተለይ በ1971 ከሦስት እስር ቤቶች ተወስደው የተገደሉ ሰዎች አፅም በሚለቀምበት ወቅት፣ በዚያ ቦታ እየተገኙ ባደረጉት ፍለጋ የሁለት ሴት የመኢሶን አመራር አባላት፣ ማለትም የዶ/ር ንግስት አዳነ እና የወ/ሪት ቆንጅት ከበደን አፅሞች ለይተው በማግኘት ለማረጋገጥ ቻሉ። የሁለቱ ጓዶችም አፅም ወላጆቻቸው ወደተቀበሩባቸው ቤተመቃብሮች ተወስደው በክብር አረፉ።
ይህንን ተከትሎ ነበር፣ በነዚሁ ሁለት ጓዶች አነሳሽነት ከጫንጮ ከተማ ምዕራብ ሰኞ ገበያ በሚባለው ስፍራ አካባቢ የወደቁትን የመኢሶን መሪዎችና ዋነኛ አባላት አፅም ያረፈበትን ቦታ ለማግኘትና አውጥቶ በክብር ለማሳረፍ ሙከራ የተጀመረው።
የዚህ ሙከራ የመጀመሪያ ክፍል፣ ጓዶቹ የወደቁበትን አካባቢ የሚያሳይ ሰው ማግኘትና በእሱ መሪነት ወደ አካባቢው ሄዶ ትክክለኛ ቦታ አግኝቶ ማረጋገጥ ነበር። ይኸን ለማድረግ ቦታውን የሚያውቀውን ሰው በመያዝ 1ኛ/ የአቶ ዳንኤል ታደሰ ባለቤት ወ/ሮ እንጉዳይ በቀለ 2ኛ/ የቅርብ ጓደኛቸው ወ/ሮ ማንያህልሻል ከበደ 3ኛ/ ፕ/ር ካሣሁን ብርሃኑ 4ኛ/ ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ እና 5ኛ/ አቶ ግርማ አለማየሁ በአንድ ላይ ሆነው ወደ አካባቢው አመሩ። በአካባቢው ደርሰው መጠያየቅ እንደጀመሩ ወዲያውኑ የአካባቢው ሰዎች ቀርበዋቸው የመጡበትን ጉዳይ ምንነት ካዳመጡ በኋላ አንዱ ሽማግሌ የሚከተለውን አሏቸው።
“እኛ የሟቾቹን ማንነት፣ ለምን ወደዚህ መጥተው እንደተሰዉ እናዉቃለን። የተቀበሩበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን የአቀባበራቸውንም ሁኔታ እናውቃለን። ምክንያቱም እኛ ራሳችን ነን የቀበርናቸው። ነገሩ እንደዚህ ነው። በነሐሴ ወር መጨረሻ እሁድ ዕለት ከዚህ ማዶ ያለ ቦታ ላይ የደርግ ወታደሮች ደርሰውባቸው ተገደሉ። ከዚያም ወታደሮቹ አስክሬናቸውን ከገደሉበት ቦታ አምጥተው ልብሳቸውን ገፈው እዚሁ ገበያችን አጠገብ ጣሏቸው። በሚቀጥለው ቀን ሰኞ ዕለት ገበያችን የሚውልበት ቀን እንደመሆኑ፣ ሕዝብ አስክሬናቸውን ያይ ዘንድ እንዳይነሳ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፈው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ሰኞ ጠዋት ሕዝቡ ወደ ገበያ መጉረፍ ሲጀምር፣ የሚያውቃቸው ሰዎች አስክሬን ጭምር እንደዚያ መውደቁን እያየ በመደንገጥ እየሸሸ ይመለስ ጀመር። የዚያን ቀን ገበያው ሳይቆም ቀረ። ወደ ማምሻው ላይ በአካባቢው የምንኖር ሰዎች፣ ለቀበሌው መሪዎች “እንዴት እንዲህ ይደረጋል? ለሰውስ ክብር ሆነ ለመጠጥ ውሃው ሲባል አፈር መልበስ የለባቸውም ወይ?” ብለን በመለመን እሺ አሰኘናቸው። ከየቤታችንም ቡቱቶ ፈላልገንና የዛፍ ልጥ እና ቅጠል ጎዝጉዘን በቆፈርነው የጋራ መቃብር አምስቱንም ሟቾች ቀበርናቸው። የሚገርመኝ ያ መልከ-መልካሙ ሚኒስትር (ዳንኤል ታደሠ) ከሞተ ከ24 ሰዓት በኋላም በሕይወት ያለ ይመስል ነበር። ከታች ዶክተሩን (ከበደ መንገሻን) ከዚያ ሚኒስትሩን፣ ቀጥሎ ደምቢ (ዲሣሣን) እና ምትኩ (ተርፋሳን) በመጨረሻም ስሙን የማናውቀውን ወጣት (ዳንኤል፤ የጄንጅስን ወንድም) አድርገን ቀበርናቸው። ከዚያም ለምልክት እና ለማስታወሻ ብለን እነዚህን እንደዚህ አድገው የምታዩዋቸውን ባህርዛፎች በክቦሺ ተከልን ። እኛ እዚህ መጥታችሁ ስላየናችሁ ደስ ብሎናል። ሌላው የደርግ ሰለባ ከየቦታው አፅሙ ሲነሳ የእነኝህ ወድቆ መቅረቱ ለምንድነው? ወገን የላቸውም ወይ? ስንል ነበር። አሁንም፣ ምንም ቢዘገይ መምጣታችሁ መልካም ነው።”
አረጋዊው ይህን ብለው እንደጨረሱ ከመካከላቸው ያሉ ሰዎች
“እንዲያውም ይኸውና ሟቾቹ በመጨረሻዋ ቀናቸው አርፈውበት የነበረው ቤት ባለቤት፤ አሁን በአጋጣሚ ዘመድ ጥየቃ መጥቶ ከነበረበት ጠርተነው መጥትዋል። እሱ የመጨረሻቸውን ታሪክ በትክክል ይንገራችሁ፣ አዳምጡት”
ብለው አንድ ሌላ አረጋዊ ሰውን አቀረቡ። ሰውዬውም ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የሚቀጥለውን የምስክርነት ቃል ሰጡ።
“እሁድ ጠዋት (ነሐሴ 3ዐ ቀን 1969) አምስቱ ሰዎች እኔ ቤት ደረሱ፣ እዚያው አርፍደው ከሰዓት በኋላ ላይ ወታደሮች ቤቱን እንደከበቡት ተረዳንና፣ ወዲያውኑ ዶክተሩና ሚኒስትሩ (ዶ/ር ከበደ መንገሻ እና አቶ ዳንኤል ታደሰ)፣ ሦስቱን ወጣቶች “እናንተ የአመራር አባላት ስላልሆናችሁ እጃችሁን ስጡና ሕይወታችሁ ይትረፍ ውጡ” አሏቸው። ከዚያም ሁለቱ “ደህና ሁን፣ ደህና ሁን” ተባብለው ሽጉጦቻቸውን ሲያነሱ፣ እኔ ደግሞ “ምነው ጌቶቼ እንዴት ራሳችሁን ታጠፋላችሁ”፣ እያልኩ ስለምናቸው፣ ሁለቱም በየሽጉጦቻቸው ጭንቅላቶቻቸውን መትተው ወደቁ። ይህ እየሆነ ሳለ ሦስቱ ወጣቶች ደግሞ እየተኮሱ ወጥተው ከባድ መትረየሶች ጠምደው ይጠብቋቸው በነበሩት ወታደሮች የጥይት እሮምታ እየተመቱ ወደቁ። ወታደሮቹ የሁሉንም አስከሬን በገበሬ አሸክመው ወደ ሰኞ ገበያ በማምጣት በዚህ ጣሏቸው።”
ከአዲስ አበባ ቦታውን በማጣራት የሄዱት ጓዶች ይህንን እንደሰሙ፣ ወዲያው በቅርብ ወደሚገኘው ጓዶቹ ወደተቀበሩበት ቦታ ከአካባቢው ሰዎች ጋር አመሩ። የአካባቢው ሕዝብም ከየአቅጣጫው እየመጣ ቁጥሩ ጨመረ። በተቀበሩበት ቦታ በክቦሺ የተተከሉት እና 12 ዓመታት ያስቆጠሩት የባህርዛፎችም እጅግ አድገው ቦታውን ልዩ ግርማ አሳድረውበት ነበር። የአካባቢው ነዋሪ ወንዶችና ሴቶችም የእንግዶቹን ማንነት ሲያውቁ እንደ አዲስ በእንባ መራጨት ጀመሩ። የአቶ ዳንኤል ታደሰ ባለቤት ወ/ሮ እንጉዳይም በመቃብራቸው ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀመጠች።
ከዚያ ጉዞ መልስ ጓዶች አፅማቸውን ከዚያ አውጥቶ በመካነ-መቃብር ለማሳረፍ ለወረዳው አስተዳደር ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ከበላይ መልስ ስለልተሰጠበት ምንም ማድረግ አይቻልም ተባሉ። ምናልባትም እነኝህ አምስት ገዶች ሙያ ሰርተው በወደቁበት መሬትና አረንጓዴ ሃውልት ባስቀመጠላቸው ሕዝብ የመኖሪያ ቦታ መቅረታቸው፣ ያምኑበት የነበረው ዓለምአቀፋዊነት፣ ያምኑበት የነበረው መላ ዓለም የሁሉም የሰው ልጆች ቤት መሆን ምስክር ሆኖ ይቀጥል ዘንድ የታሪክ መልካም ፈቃድ ሁን ያለው መደምደሚያ ይኸኛው ይሆናልና፤ ይሁን!
(የእነ ዶ/ር ከበደ መንገሻን አጽም ለመፈለግ ከሄዱት ጓዶች አንዱ)
በጎንድር ክ/ሃገር በመኢ ሶን አባላት ፤ካድሬዎችና ደጋፊዎች ላይ በተደረገው ጭፍጨፋ የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር
በክፍ ለሃገሩ በመኢሶን ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከሌሎች ክ/ሃገራት ለየት ባለና በከፋ መልክ ነበር። አብዛኛው ግድያ በቀጥታ በደርግና በኢህ አፓ የተፈጸመ ቢሆንም ኢህአፓ በደርግና በህዝብ ድርጅት ይባል በነበረው ሰርጎ በመግባት ግድያ የተካሄደ ሲሆን ኢዲዩ እና ቲፒኤሌፍ የተባሉትም የበኩላቸውን አሰቃቂ ግድያ አከናውነዋል። ለግንዛቤ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፤ በጎንደር ክ/ሃገር የድርግ አባል የነበረውና በጭካኔው ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሻለቃ መላኩ ተፈራ ይመራው የነበረው በፊት መንጥር በኋላ ደግሞ መብረቅ የሚባል ወታደራዊ የጦር ፍ/ቤት ነበረው። በዚህ ኮሚቴ ተሳታፊ የነበሩት ህዝብ ድርጅት ጽ/ቤት ፤ የጎንደር ከተማ ከንቲባና ምክትሉ ፤የክ/ሃገሩ ፖሊስ ተወካይና ከጦሩ አንድ ተወካይ ይሳተፉ እንደበበር ምስጢር አልነበረም።
የዚህ የቀይ ሽብር ኮሚቴ የራሱ የምርመራ ቡድንና ቀይ ሽብሩን የሚፈጽሙ ምርጥ ቅልብ ስፔሽያሊስቶች ነበሩት። የቡድኑ ሰብሳቢ መነላኩ ተፈራ ቢሆንም ኢህአፓ ደግሞ በራሱ ፍርድ ፊት
ለፊት ከሚገድለው በተጨማሪ በጣም በረቀቀና በሚስጢር ሰርጎ በመግባት በኮሚቴው ውስጥ ቢያንስ ሁለት አባላት ነበሩት።
…..በ1970 መጨረሻ በደርግ መፈክር” ደም ስጡ ደም እንስጥ” በሚለው መፈክር መሰረት በአረመኔው መላኩ ተፈራ በሚመራው መብረቅ በተሰኘው ኮሚቴ ውሳኔ መሰረት እጅ
እግራቸውና መላ ሰውነታቸው በቶርች ወንበር ተጠርፎ እየታሰረ በጤና ጥበቃ ሰራተኞች ደማቸው ተሟጦ ከተወሰደ በኋላ በጀምላ አዘዞ ከተማ በሚገኘው የጀምላ የቀይ ሽብር መቃብር ተቀብረዋል።
አንዲት ወጣት የመኢሶን ካድሬ ጓደኛ ነች ተብላ በመጠርጠሯ ብቻ በኢህአፓ ጓደኞቿ
የይስሙላ ፓርቲ ተጠርታ ከሄደች በኋላ በኢህአፓ ውሳኔ በገመድ ተንጠልጥላ ተገድላለች።
…..በጎንደር ክ/ሃገር ደንቀዝ በሚባል ቦታ እጅግ ዝነኛ፤ ታዋቂና የተከበረ ገበሬ የነበር፣
የእህቱ ልጅ የመኢሶን ካድሬ በመሆኑ ምክንያት ህዝብን በመንግስት ላይ ሊያነሳሳ ይችላል ተብሎ በመኢሶን ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ህዳር 1970 ከሌሎች አራት ገበሬዎች ጋር ጎንደር ከተማ አካባቢ ከምትገኘው ጠዳ ከተማ ላይ ለገብያ የመጣው ህዝብ እያየ በመላኩ ገዳይ ቡድን በጠራራ ጸሃይ በጥይት ተጨፍጭፈው ሬሳቸው ሳይነሳ እንዲውል ተደርጓል።
(ጎንደር የነበረ የመኢሶን አባል ምስክርነት)
ሰላም የተከበራችሁ የመኢሶን ቤተሰቦች !
ከዛሬ 50 አመት በፊት በሃገራችን የሆነውን የየካቲቱን ሥር ነቀል አብዮት በማስታወስ ከዚሁ ታሪክ ጋር የተሳሰረውን የመኢሶን ሰማእታት በማሰብም መዘከሩ ፍጹም ተገቢና ትክክል ስራ ነው። አስባችሁ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ይህንን የሰማታት መጽህፍ አዘጋጅታችሁ ከማበርከታችሁም አልፎ ይህንን እለት ለመዘከር እንድንሰባሰብ በማድረጋችሁ አዘጋጆቹ ጓዶቻችን ፍጹም የከበረ ምስጋና ይድረሳችሁ ።
ለየካቲቱ አብዮት መከሰት ከአብዮቱ በፊት የነበረ ችግሮች ሚና እንደነበራቸው ይታወሳል። የፍትህ እጦት፣ የአስተዳደር በደል፣ ርሃብ፣ የመሳሰሉት ችግሮች ሁሉ ተደማምሮ ሚሊዮን አርሶ አደሮችን፣ ሠራተኛውን፣ ተማሪውን፣ ሠራዊቱን፣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችንና እንዲሁም በከተማ ታክሲ ነጂዎችን፣ አስተማሪዎችን ሁሉ አነቃንቆ ብሶታቸውን አንግበው በመነሳት ያመጡት የለውጥ ማእበል ነው። ይህም የየካቲቱ አብዮት ይባላል።
ይህንን ሁሉ የምታውቁትን ሃተታ መዘርዘሬ በተሳሳተ ትረካ ዛሬ ይህንን ሃቅ ክደውና ቀጥፈው የዚያን ጊዜ ትውልድ አሲሮ ያመጣው ክስተት ሲሉ ስለምሰማ ነው። የየካቲቱን አብዮት ያ ትውልድ አልፈጠረውም። አልመራውም፣ የመንግስት ሥልጣን ጨብጦም አላስተዳደረውም።
የ66ቱ አብዮት ዛሬ ጊዜው ርቆ ደብዘዝ ብሎ ደምቆ ባይታይም አለም ላይ ከተካሄዱ ጥቂት አብዮቶች የሚመደብ እንደሆነ በሰፊው የተነገረለት ነው። እጅግ ሥር ነቀል ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ የነበረውን ስርአት አድሶ አዲስ ስርአት የማዋቀር አላማም ይዞ እንደነበርም ይታወሳል። የየካቲቱ አብዮት ኢትዮጵያዊያን በጋራ ያመጡት ድል ነው። ታላቅ የሆነ የታሪክ ምእራፍ ነው።
የየካቲቱ አብዮት በፈጠረው ክስተት ተያይዞ ዛሬ የምንዘከረው የዚያ ትውልድ አስተዋጾም በተለይም ለውጡ ግቡን እንዲመታ የአደረገው ትግል ሊነገርም፣ ሊወደስም ይገባዋል። የሃገራቸውን ኋላቀርነት ተቆጭተው ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነበት፣ ዲሞክራሲ ሥርአት ለማነጽ ቃልኪዳናቸውን አክብረው እነዚህ የመኢሶን ሰማእታት ለብሩህ ራእይ፣ ህልማቸው በመታገል ህይወታቸውን ለግሰዋል። ለተበደሉና ፍትህ ላጡ ወገኖች በጽናት ቆመው አልፈዋል። ይህ ታሪካቸው በኢትዮጵያ ብርሃን ሲያይ ደምቆ እንደሚቀር አያጠራጥርም። እኛም ዛሬ ስንዘክራቸው፣ ዛሬም ያልረሳናቸው በውስጣችን ያሉ መሆኑ በሚገባ ሊታወቅ ይገባል። አንዳንዶቻችሁም እዚህ ዛሬ የታደማችሁ ከእስር ቤት ከጒናችሁ አጣድፈው ለግድያ ሲወስዷቸው ለመጨረሻ በአይናቸው ሰርቀው ተሰናብተዋችሁ ሲለያችሁ መቼ ይሆን ቀጣዩ ተራዬ ብላችሁ የተረፋችሁ ያ የጨለማና የሰቀቀን ገጽታ፣ ዛሬም እንደሚታወሳችሁ፤ አልፎ ተርፎም ቀሪ መስካሪም ናችሁ።
እነዚህ የመኢሶን ሰማእታት የታገሉለት አላማ ተደናቅፎና ግብ መቶ ባይሳካም በአደረጉት የአጭር ጊዜ ተጋድሎ በቀላሉ የማይገመት ውጤቶችም አስገኝተው አልፈዋል። የታገሉለት አላማ ጭሰኝነት፣ ገባርነትን አላቋል። የሃይማኖት ፣ የብሄር እኩልነት እንዲታወቅ በር ከፍቷል። የፊውዳሉን የዘውድ አገዛዝ ሥርአት አፍርሷል።
የየካቲቱን የታሪክ ምእራፍ ማክበር ሲታሰብ በቅርቡ በተዛባ ትርካት በቦታው ያልነበሩ አስመሳዮች በደፈናው ምንም እንኳን ግራጫ ገጽታ እንዳለው ቢታውቅም በማጉደፍ ስለው ሲዘምቱ መስማትም ችለናል። ያ! ትውልድ ያ! ዘመን እየተባለ በተዛባ አነጋገር የሚሰጠው ትርካት በማስተካከል ሃቅን ማስተላለፍ ይገባል። መጭው ትውልድ የትላንቱን በውል አውቆ
ከዚያም ተምሮ ወደ ተሻለ ለመሻገር እነዚህ የመኢሶን ሰማእታት የተጓዙበት ታሪክ ሂደት በስፋትም ፣በጥልቀትም ለማውቅ ይህ መጽሃፍ አይነተኛ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል። ወደፊትም ስለ ሰማእታቱ ብዙ ያልተነገሩ በየጓዳችን ያሉ ታሪኮች፣ ሰነዶች ተልቃቅሞ በቀጣይ እትምት የሚታከሉበት መላ መፍጠሩ ይታሰብበት በሚል በዚህ አጋጣሚ ሃሳቤን አቀርባለሁ።
(የመኢሶንን ሰማዕታት ለመዘከር የተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ከተነበቡ አስተያየቶች መሃል)
Remembering My Dad Daniel Tadesse
As Daniel Tadesse’s child, I’ve often wondered about the legacy my father left behind. I think it’s fair to say that it’s a precious legacy, made up of stories of heroic deeds, courage and sacrifice, but also a psychological legacy that has deeply affected our family. For me, this legacy has many facets, from inspiration and pride to emotional challenges and profound questions of values and worldview. The example of determination and courage set by Daniel Tadesse and other members of my family is a source of pride and inspiration for me. I can say that integrity and sincerity of
commitment are examples that I was given to follow very early in my childhood. I have also inherited a deep trauma and complex grief given the circumstances in which Daniel Tadesse and other members of my family died, as well as the difficult conditions my mother Engudai Bekele had to face in our childhood. This situation was exacerbated by the fact that the expression of sadness and pain was itself restrained. The way my family members faced adversity, following the disappearances of my father Daniel Tadesse, my uncle Desta Tadesse and my aunt Dr Nigist Adane and their comrades, has always been very dignified and is also part of my heritage. Early on, I felt the need to live up to my family history, to perpetuate the legacy and to live by the examples I was given to see.
I thank my mother Engudai Bekele, my grandparents W/ro Fantaye Ruphael and Fitawrari Tadesse Markos and my aunt Zenebework Tadesse for being the guardians of my father’s memory. As Victor Hugo said, “Remembrance is the invisible presence”. They brought Daniel Tadesse’s memory to life in our children’s eyes and gave us a unique legacy. I would also like to thank those responsible for this memorial project. The publication of this book will enable us to pay a well-deserved tribute to people who demonstrated courageous acts and sacrifices for ideals they felt were right.
The losses were considerable, and our duty is to remember and pass on to future generations. Passing on to help preserve peace and justice, while contributing to the prevention of past mistakes. Pass it on as a commitment to a better future, where the lessons of the past are used to guide present and future actions.
In Memory of My Beloved Father
My dad, Terefe Woldetsadik, was born in Woliso, Shewa province. He completed his early elementary education in Woliso while living with his single mom and four siblings (two brothers and two sisters). He was the third child. He moved to Addis Ababa at an early age to continue his education and attended Ameha Desta, where he completed high school. I was told that my dad was highly regarded at Ameha Desta, and both he and Gash Lemma Argaw served on the student council as president and secretary, respectively, until they completed high school. After graduating, both continued their higher education at Addis Ababa University (AAU).
My mom, Atnaf-Alem Yemam, attended Woizero Sehin School in Dessie, Wello province, where she completed her elementary education. She then moved to Addis Ababa and joined Etege Menen boarding school, where she completed high school.
My parents met at AAU and graduated together in 1964. They got married while my dad was still working at AAU as a student public relations director for one year. Their wedding ceremony took place at the AAU’s student hall, according to Auntie Aslaku and both my late uncles. The wedding was expedited because my dad had received a scholarship from ISS University in the Netherlands and decided to take my mom along with him.
The one thing I loved most about my parents, and have always been proud of, especially about my dad, is that besides his strength in the academic world, he genuinely loved and cared for people who were less fortunate.
For instance, although I was told about many of my dad’s great qualities, the story that resonates with me the most is that he used to give the people who worked in our household as a security guard and maid the opportunity to attend night school. He even let our security guard, Mulugeta, work at the የካቲት 66 የፖለቲካ ትምህርት ቤት (Yekatit 66 Political School) during the day while living with us and performing his duties as a security guard at night alongside my uncles at our ባምቢስ home, where we were living at the time. I think this fact deserves to be mentioned in my own writing if I find the strength to do that!
Years later, after both my parents were assassinated by the Derg, both Mulugeta and our former home helper, who became Mulugeta’s wife, came to Auntie Aslaku’s home to visit me and shared their personal testimonies about what kind of people my late parents were.
In Memory of My Beloved Mother
Atnaf-Alem Yemame was born on November 21, 1945 G.C. (Hedar 18, 1938 Eth.C.) in Dessie, Wollo, Ethiopia. She began her early education in Dessie at the Empress Menene Elementary School, where she completed her elementary education in 1951 Eth.C. She then moved to Addis Ababa to further her education at the Empress Menen Secondary School, graduating in 1954 Eth.C. From 1955 to 1959 Eth.C., she continued her higher education at Haile Selassie I University in Addis Ababa, where she received her diploma from the School of Social Work. It was during her time at Haile Selassie I University that she met her college sweetheart, my dad, Dr. Terrefe Woldetsadik (one of the founders of the All Ethiopian Socialist Movement [Meison]), whom she married in the early 1960s Eth.C.
In August 1968 G.C., my mom and dad both went to The Hague, Netherlands, to continue their higher education at the Institute of Social Studies (ISS). My mom received her degree in Urban Social Development on June 29, 1973, followed by her master’s degree in social science on September 4, 1974.
My mom is survived by her two children: me, Gashu Terrefe Woldetsadik (born on August 10, 1970 G.C. in The Hague, Netherlands), and Tekalegn Terrefe Woldetsadik (born on February 28, 1977 G.C. in Addis Ababa and deceased on August 7, 2003 G.C.). May he rest in peace and rise in glory.
My mom was murdered by the Derg regime’s hit squad alongside my dad in December 1978 G.C. (early Tahesas 1970s Eth.C.), leaving behind her two children (7 years old and 5 months old at the time). Currently, the only survivor of the Terrefe family is me, Gashu Terrefe, who has lived in the United States of America since November 26, 1990 G.C., in Maryland State with my wife. Both my dad and mom would have been grandparents to three children: my two children, Matthewos Gashu Terrefe, 20, and Yonathan Gashu Terrefe, 18, as well as my brother Tekalegn’s son, Matthew Tekalegn Terrefe, 22, who lives in Addis Ababa.
My mom was a brave and patriotic Ethiopian woman who sacrificed her life fighting for a great cause alongside her beloved husband, Dr. Terrefe, my dad, and nine other fellow MEISON active members near Ambo town, in west-central Ethiopia, in December 1978 Eth.C. She is always remembered by her children and her siblings as a courageous mother who loved her country and for her altruism and devotion as a social worker to always help those members of our society who were in dire need.
May both my parents rest in peace.
ዶ/ር ንግስት አዳነ
ዶር ንግስት አዳነ በጣም የምወዳትና የማከብራት ጓደኛዬ ናት። ከሩቁ ስትታይ ገፅታዋ የሚያስፈራ ቢመስልም ሲቀርቧት ግን በጣም ተግባቢ ቀልደኛና ደግ ሰው ነች። በተጨማሪም ትጉህ ሰራተኛ ብልህ መፅሀፍ አንባቢና ከባድ የሆኑ አስተሳሰቦችን በቀላል ቃላት የምታስረዳ ለአመነችበት ከልቧ የምትሰራ ቆሬጥ ጠንካራ ጓድ ነበረች ።
የመኢሶን የሴቶች ድርጅት በተመሰረተበት ስብሰባ ላይ በመሪነት፣ በአስተማሪነትና የሁሉንም ሃሳብ በማዳመጥ በተነሱት ሃሳቦች ላይ ስምምምንት ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት ታደርግ ነበር።
ምን ያህል ቆራጥ እንደሆነች አንድ ምሳሌ ልስጥ –
ከርቸሌ በነበርንበት ጊዜ በየአመቱ ምዝገባ ይደረግ ነበር ።ስም እድሜ ከተሞላ በኋላ “የታሰርሽበትን ስራ የሰራሽው አውቀሽ ነው ወይስ ተወናብደሽ ነው” የሚል ጥያቄ ይቀርባል። እኔ እስከማውቀው ድረስ ከንግስት በስተቀር “አውቄ ነው“ ብሎ የሚመልስ ማንም የለም። ነገር ያከብዱባታል ብየ ስለምፈራ አንድ ቀን “ንግስት ምን ቸገረሽ ተወናብጀ ነው” በያቸው አልኳት። እሷም “ከዚያስ ማን አወናበደኝ ልበል” አለችኝ ።
ሌላ ደግሞ ለልጇ ለሀዲስ የነበራትን ፍቅርና ናፍቆት አስታውሳለሁ። አንድ ጊዜ ለልደቱ የሳንቲም መያዣ ቦርሳ ለመስራት የማታውቅበትን ዳንቴል መስራት እንደምንም ተለማምዳ ሰርታ ስትጨርስ የተሰማት ደስታ አይረሳኝም።
በእስር ቤት በነበረችበት ጊዜ ምግብ አብረን ስንመገብ አዘጋጅና አቅራቢ በተራ ነበር ።ንግሥት ተረኛ በሆነችበት ቀን በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ሌሎቻችን በተራችን የመጣውን ምግብ አሙቆ ከማቅረብ የበለጠ አናደርግም። በሷ ተራ ጊዜ ግን የምንጠቀምባቸው እቃዎች በሙሉ እስኪያብረቀርቡ ታጥበው ሁሉ ዕቃ ተስተካክሎ ይቀመጣል ።