ፈቃዱ ሩጋ
ፈቃዱ ሩጋ፣ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዘርፍ ምሩቅ ነበር። አዲስ አበባ መድኃኔ ዓለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በርዕሰ መምህርነት ያገለግል የነበረ የመኢሶን አባልም ነበር።
የአብዮቱ ደጋፊና የመኢሶን አባል በመሆኑ፣ ሐምሌ 9 ቀን 1969 ዓ.ም. ምሽት ላይ የኢሕአፓ ነፍሰ ገዳይ ቡድን አባሎች፣ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ፣ በፈቃዱና በቤተሰቡ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ግድያ ፈጸሙ።
ከፈቃዱ ሌላ በወቅቱ አብረውት ቤቱ ውስጥ የነበሩትን የሰባ አራት ዓመት አዛውንት አባቱንና የአሥራ አራት ዓመት ታዳጊ ልጁን ጭምር በጭካኔ ገደሉ። በተጨማሪም አብራ የነበረችውን እህቱን አቆሰሉ።
ፈቃዱ ሩጋን በኮሌጅ ትምህርት ዘመኑ የሚያውቁት በተጫዋችነቱ፣ ከሰው ጋር በቀላሉ በመግባባት ባህሪውና በስፖርት ወዳድነቱ ያስታውሱታል።