ዳምጤ ጎበዜ
ዳምጤ ጎበዜ፣ በወሎ ክፍለ አገር ጀብል የሚባል ቦታ በ1950 ዓ.ም. ተወለደ። ወላጅ እናቱ ልጃቸው እንዲማርላቸው በነበራቸው ጉጉት ትምህርቱን ለመከታተል እንዲያመቸው አዲስ አበባ በሚኖሩት በአጎቱ በአቶ ጎበዜ ጣፈጠ ቤት ተቀምጦ አንዲማር አደረጉ። ዳምጤም በአሥር ዓመቱ በአምሃ ደስታ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርቱን ጀመረ። በትምህርቱ ጎበዝ ተማሪ ስለነበረ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በአምስት ዓመት አጠናቅቆ ተፈሪ መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ገባ። አዚያም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ እያለ በ1970 ዓ/ም በጥቅምት ወር፣ ከቤት ወጥቶ ወደ ት/ቤት እየሄደ ሳለ፣ ስዊድን ሚሽን ት/ቤት በር ላይ ከአንድ የኢሕአፓ ነፍሰ ገዳይ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱ አለፈ።
ዳምጤ ጎበዝ ተማሪ ነበር። ከዚያም በላይ፣ ተፈሪ መኮንን ተማሪ በነበረበት ወቅት በውይይት ክበብና በአጠቀላይ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ ያደርግ ነበር። በተጨማሪም የመኢሶን ወጣት ክንፍ ወስጥ በኅቡዕ ይንቀሳቀስ የነበረ ጓድ ነበር።
ዳምጤ ሕይወቱ ሲያልፍ ሃያ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ይቀሩት ነበር።