ኩመላ ካሮርሳ
ኩመላ ካሮርሳ በጅባትና ሜጫ አውራጃ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ያገለግል የነበረ የመኢሶን ጓድ ነበር። በ1969 ዓ.ም. ነሐሴ ወር መኢሶን የትግል ስልት ለውጥ ሲያደርግ፣ በጅባትና ሜጫ አውራጃ ከተመደቡት ጓዶች ጋር ትግሉን በኅቡዕ ያካሂዱ ከነበሩ መሃል አንዱ ነበር።
ምዕራብ ሸዋ፣ ጊንጪ አጠገብ ደንዲ ወረዳ በዶ/ር ተረፈ የሚመራው ቡድን በኅቡዕ ይኖርበት የነበረውን ቤት የሚያውቁና በአገናኝነት ይሠሩ የነበሩ ሁለት የጅባትና ሜጫ አውራጃ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ባልደረቦች በፈጸሙት ክሕደት ጓዶቹ በድብቅ የሚኖሩበት ቦታ ምስጢር ደርግ እጅ ገባ። ከዚያም፣ ከደርግ ጽ/ቤት የመጣ ልዩ ኃይል፣ በነዚህ ሁለት ከሃዲዎች እየተመራ ቤቱን ሲከብ ጓዶቹ እጃቸውን ለመስጠት ተገደዱ።
የዓይን እማኞች እንደመሰከሩት፣ ኩመላ ካሮርሳንም ከነርሱ ጋር ደባልቀው ያለምንም ፍርድ በጭካኔ ረሸኑት።