ለማ ፊዳ
ለማ ፊዳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ይከታተል የነበረ የመኢሶን አባል ነበር። በ1969 ዓ.ም. ነሐሴ ወር፣ መኢሶን የትግል ለውጥ ሲያደርግ፣ በጅባትና ሜጫ አውራጃ ትግሉን በኅቡዕ እንዲቀጥሉ ከተመደቡ ጓዶች መሃል አንዱ ለማ ነበር። ጅባትና ሜጫ በዶ/ር ተረፈ ወልደ ፃዲቅ ይመራ የነበረው ቡድን በኅቡዕ ይኖርበት የነበረውን ቤት የሚያውቁና በአገናኝነት ይሠሩ የነበሩ ሁለት ከሐዲ የጅባትና ሜጫ አውራጃው የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ባልደረቦች ከደርግ ጽ/ቤት ለመጣው ልዩ መቺ ኃይል ቤቱን ጠቆሙ። ምንም እንኳን ልዩ ኃይሉ ቤቱን ከከበበው በኋላ ጓዶቹ እጃቸውን ቢሰጡም፣ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል በእግር እንዲጓዙ ተደርጎ እዚያው ሁሉንም ረሸኗቸው።
የዚህ ቡደን አባል የነበረው ወጣቱ ለማ ፊዳም በዚሁ የጭካኔ ግድያ ሕይወቱ አለፈች።