አሰፋ መኮንን

አሰፋ መኮንን በጎንደር ክፍለ አገር  ደንቀዝ በተባለ ስፍራ እጅግ ታዋቂና የተከበረ ገበሬ ነበር። የእህቱ ልጅ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ካድሬ ስለነበረ በመኢሶን ደጋፊነት ተጠርጥሮ ታሰረ። በኅዳር ወር 1970 ዓ.ም. የደርግ አባልና የጎንደር ክ/አገር አስተዳዳሪ በነበረው በሻለቃ መላኩ ተፈራ ትእዛዝ ከሌሎች አራት ገበሬዎች ጋር ጎንደር አጠገብ ጠዳ ከተማ ላይ ለገበያ የመጣ ሕዝብ በተሰበሰበበት በጥይት ተደብድቦ ተገደለ:: አስከሬኑም ሳይነሳ እንዲውል ተደረገ።

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top