አንዱዓለም ታምራት አንዱዓለም ታምራት፣ በፍልውኃ አስተዳደር፣ የፍልውኃ ሠራተኞች ማኅበር የውይይት ኮሚቴ ሊቀ መንበርና የመኢሶን አባል ነበር። ከሰዎች ጋር እጀግ ተግባቢና ሰው አፍቃሪ ነበር። አንዱዓለም ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ውስጥ ቡልጋሪያ ኤምባሲ አካባቢ ነበር። ጥቅምት 4፣ 1970 ዓ.ም. አዲስ አበባ በአዲሱ ፍልውኃ መሥሪያ ቤቱ ደጃፍ ላይ፣ በኢሕአፓ ነፍሰ ገዳዮች በደፈጣ ተገደለ።