እምሩ ኢብሳ

እምሩ ኢብሳ በ1931 ዓ.ም. ጅማ ገነቲ ፣ ሰላን የተባለ ቦታ ተወለደ። በቀድሞው አጠራር፣ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በጂኦግራፊ ተመረቀ። ከዚያም ከታወቀው ከኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በመሬት አያያዝ የድሀረ ምረቃ ዲፕሎማ አገኘ።

ትምህርቱን ከአጠናቀቀ በኋላ በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች አገልግሏል። በመጨረሻም የሆሮ ጉዱሩ አውራጃ አስተዳዳሪ ሆኖ ሠርቷል። አውራጃ አስተዳዳሪ በነበረበት ወቅት በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ ከመሆኑ ሌላ፣ በ1967 ዓ.ም. የታወጀው የገጠር የመሬት አዋጅ በሥራ ላይ እንዲውል በአካባቢው ከነበሩ ገበሬዎች፣ ተማሪዎችና ተራማጅ ኃይሎች ጋር ተባብሮ በመሥራት ይታወቅ ነበር።

መኢሶን በ1969 ዓ.ም.  ነሓሴ አጋማሽ ላይ የትግል ስልት ለውጥ ሲያደርግ፣ እምሩ በደርግ መንግሥት ተወካይ በነበረው ንጉሴ በሚባል የደርግ አባል ትዕዛዝ ታሰረ። እጀግ አስከፊ በሆነው በነቀምቴ ጃቶ እስር ቤት ሲንገላታና ሲሰቃይ ከከረመ በኋላ መስከረም 2 ቀን፣ 1972 ዓ.ም ከሌሎች የመኢሶን ጓዶች፣ ከብሩ ወርቁና ክፋሪስ ሂርጳ ጋር በአንድነት በግፍ ተረሸነ።

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top