አቡበከር አብዱል መጂድ

አቡበከር አብዱል መጂድ፣ አዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አዲስ አበባ በሚገኘው በወቅቱ መርካቶ አካባቢ ልዑል መኮንን ተብሎ ይጠራ በነበረው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀቀ። በመቀጠልም በማስታወቂያ ሚኒስቴር ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ። በስፖርት ጎበዝ የተባለ የእግር ኳስ ተጫዋችም ነበር።

አቡበከር፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ግቡን ይመታ ዘንድ ጽኑ ፍላጎት ነበረው። ለዚህም ሕዝባዊ ለውጥ መሳካት፣ ወጣቶችን በማንቃትና በማደራጀት የትግል ድርሻውን ሳያሰልስ ያበረክት ነበር። መስከረም 17 ቀን፣ 1969 ዓ.ም. መርካቶ ውስጥ በአንዲት ክፍል ውስጥ ተሰብስበው የፖለቲካ ጥናት በማካሄድ ላይ እያሉ ከሁለት የቅርብ ጓዶቹ ከገብረ እግዚአብሔር ተስፋይ እና ከክንፈ አስፋው ጋር በኢሕአፓ ነፍሰ ገዳዮች ቡድን የጥቃት ኢላማ ሆኖ ሕይወታቸው በለጋ እድሜአቸው ከተቀጠፈው የመጀመሪያዎቹ አብዮታዊ ወጣቶች መሃል አንዱ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top