ወይንሸት ኃይለ ሥላሴ አዲስ አበባ ከተማ፣ በተለምዶ ሰንጋ ተራ በመባል የሚታወቀው ሰፈር ነዋሪ ነበረች። በመኖሪያዋ በከፍተኛ 6 ቀበሌ 53፣ የቀበሌ ማኅበር ተመራጭ ሆና በማገልገል ላይ እያለች መጋቢት 6 ቀን፣ 1969 ዓ.ም. በኢሕአፓ ነፍሰ ገዳይ ሕይወቷ ተቀጥፏል። በወቅቱ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒሰቴር ባልደረባ ነበረች። ወይንሸት፣ ረጋ ያለች፣ ጭምት፣ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች እናት ነበረች።