መኳንንት ግርማ
መኳንንት ግርማ፣ በመኢሶን ወጣት ክንፍ – የኢትዮጵያ ወጣቶች አብዮታዊ ንቅናቄ (ኢአወን) ውስጥ አባል ሆኖ ይታገል ነበር። መኳንንት ብሩህ አዕምሮ የነበረው፣ በትምህርቱም የተደነቀ እና በጠባዩ እጅግ የተመሰገነ ወጣት ነበር። መኳንንት፣ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነፋስ ስልክ ነበር።
ከየካቲት 1969 ዓ.ም. ጀምሮ በደርግ ወስጥ ጠንከሮ የወጣው “ሰደድ” ተብሎ ይጠራ የነበረው ድርጅት አባል የነበረ ካድሬ የያዘው ካላሺንኮቭ ጠመንጃ ባረቀብኝ በሚል ሰበብ መኳንንት ላይ ብዙ ጥይት አርከፈከፈበት። ገዳዩ “በስሕተት” ነው ቢልም፣ ግድያው ሆን ተብሎ የተፈጸመ የደርግ ግድያ እንደነበረ አያጠራጥርም።
ጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት ተማሪ እያለ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ያስመዘግብ የነበረውና ከሰው ጋር እጅግ በመግባባት የሚታወሰው መኳንንት ግርማ አገሩን የማገልገልና ለወገኑ ለመታገል የነበረው ምኞት በደርግ ነፍሰ ገዳይ በለጋ ዕድሜው በአጭር ተቀጨ።