ፋንቱ አበራ

ፋንቱ አበራ የተወለደው ዓዲ አርቃይ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አቋርጦ፣ በጎንደር ከተማ በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ውስጥ ማገልገል ጀመረ። ከዚያም የመኢሶንን የትግል ስልት ለውጥ ተከትሎ ታስሮ እስር ቤት ብዙ ስቃይ ደረሰበት።  ጥቅምት 4 ቀን 1970 ዓ.ም.  በደርግ አባልና የጎንደር ክፍለ አገር  ዋና አስተዳዳሪ በነበረው በሻለቃ መላኩ ተፈራ ትዕዛዝ ከወንድሙ ከዳኘ አበራ እና ከሌሎች አምስት የመኢሶን ጓዶች ጋር ያለ ምንም ፍርድ፣ ግፍ በተሞላበት አኳኋን ደሙ ተቀድቶ ተገደለ። ከዚያም በአዘዞ ከተማ የጅምላ መቃብር ተጣለ።

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top