መክሊት ግርማ

መክሊት ግርማ፣ ወጣት ተማሪ ነበረች። በጅባትና ሜጫ አውራጃ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ውስጥ የአስፋው ሽፈራው ረዳት ባልደረባ ሆና ትሠራ ነበር። መክሊት፣ በተለይ ወጣቶችንና ሴቶችን በመኢሶን የወጣቶችና የሴቶች ድርጅቶች ዙሪያ ደጋፊዎችና አባሎች ለማፍራት በማንቃትና በማደራጀት ተግታ ትሠራ ነበር። መኢሶን፣ ነሐሴ አጋማሽ 1969 ዓ.ም. የትግል ስልት ለውጥ ካደረገ ከጥቂት ወራት በኋላ ግን፣ መክሊት በደርግ ታሠረች። በ1970 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ፣ ከእስር ቤት ተወስዳ በደርግ መንግሥት ያለፍርድ ተገደለች።

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top