ብሩ ወርቁ

ብሩ ወርቁ ወለጋ ክፍለ አገር በሆሮ አውራጃ፣ አካጂ ቀበሌ ገረን ኮንሶ በሚባል ቦታ ከአባቱ ከአቶ ወርቁ ቂጤሳና ከ እናቱ ወ/ሮ ቱርቱ ዲንሳ በ1934 ዓ.ም. ተወለደ። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከአጠናቀቀ በኋላ ሐረር መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ገብቶ ትምህርቱን አጠናቀቀ። ከዚያም በወለጋ አርጆ መኮና፣ አኖ በመምህርነት አገልግሏል።  

ለጥቂት አመታት በመምህርነት ከአገለገለ በኋላ፣ በ1963 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ገባ። ወቅቱ የተማሪዎች ማኅበር ሊቀመንበር የነበረው ጥላሁን ግዛው የተገደለበት ጊዜ ነበር። ብሩም በጊዜው ተጋግሎ በተነሳው የተማሪዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት ተሳትፏል። በዚያው ዓመትም ትምህርቱን ለማቋረጥ ስለተገደደ፣ በወለጋ ሻምቡ በአቤ ደንጎሮ ት/ቤት በመምህርነት ተቀጥሮ መሥራት ጀመረ። ከዚያም በመቀጠል አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመልሶ ትምህርቱን ሲከታተል ከቆየ በኋላ በ1967 ዓ.ም. በእድገት በህብረት ዘመቻ ተሳትፏል።

በኢትዮጵያ ገጠር፣ መሬትን ለአራሹ ያደረገውን አዋጅ በሥራ ላይ ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴም፣ ብሩ ወርቁ የመሬታ ይዞታ ሚኒስቴር ተጠሪ በመሆን በሊሙ ወረዳና በሆሮ አውራጃዎች ገበሬዎችን በማደራጀትና አዋጁን ሥራ ላይ በማዋል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።            

                             

ብሩ ሕይወቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰዋ ታጋይ የመኢሶን አባል ነበር። ኅዳር 13፣ 1970 ዓ.ም. መደበኛ ሥራውን በማኪያሄድ ላይ እያለ በደርግ ወታደሮች   ተይዞ ሁለት ዓመታት በእስር ቤት ተሰቃየ። ከአካል ድብደባና ስቃይ በኋላ፣ እርሱንና ሁለት ጓዶቹን – እምሩ ኢብሳንና ፋሪስ ሂርጳን –  ደርግ ከእስር ቤት አውጥቶ ገደላቸው።

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top