ጌታሁን ታመነ
ጌታሁን ታመነ፣ ከአባቱ ከአቶ ታመነ ሥዩም እና ከእናቱ ከወ/ሮ ንግሥቲ መኮንን በ1949 ዓ.ም. አዲስ አበባ በአቧሬ አካባቢ ተወለደ። በሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአሥራ አንደኛ ክፍል ወጣት ተማሪ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪም ሳለ፣ በወጣቱ ክንፍ አማካኝነት የመኢሶን አባል ነበር።
የካቲት 12፣ 1969 ዓም፣ አዲስ አበባ ኦርማ ጋራዥ አጠገብ ከገሠሠ በላይ ጋር ውድቀት ሌሊት በተኛበት ቤት ውስጥ፣ በኢሕአፓ ታጣቂ ነፍሰ ገዳይ ቡድን ተገደለ።
ጌታሁን፣ ሲገደል የሃያ አመት ለጋ ወጣት ነበር። ጌታሁን፣ በባህሪው እጅግ ረጋ ያለ፣ ትሁትና ለእውቀት እጅግ ጉጉት የነበረው ወጣት ተማሪ ነበር።