ዲማ ጉዲና
ዲማ ጉዲና በጅባትና ሜጫ አውራጃ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ያገለግል የነበረ የመኢሶን ጓድ ነበር። በ1969 ነሐሴ ወር መኢሶን የትግል ስልት ለውጥ ሲያደርግ፣ በዚሁ አውራጃ ከተመደቡት ጓዶች መሃል አንዱ ነበር።
ምዕራብ ሸዋ፣ ጊንጪ አጠገብ ደንዲ ወረዳ በዶ/ር ተረፈ የሚመራው ቡድን በኅቡዕ ይኖርበት የነበረውን ቤት የሚያውቁና በአገናኝነት ይሠሩ የነበሩ ሁለት ከሃዲ የጅባትና ሜጫ አውራጃ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ባልደረቦች ቦታውን ለደርግ ጠቆሙ። ቀደም ሲል ተይዞ የነበረው ዲማ ጉዲና ግን በጥይት አቁስለው ቢያስፈራሩትም፣ ቦታውን ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም። በ1970 ዓ.ም. ታኅሣሥ፣ የእነ ዶ/ር ተረፈ ቡድን ተይዞ በጅምላ ሲረሸን ዲማንም ደባልቀው ከለምንም ፍርድ በጭካኔ ገደሉት።
ዲማ ለዓላማው የሚቆም መንፈሰ ቆራጥ ጓድ ነበር።