መለሰ መልካሙ መለሰ የተወለደው ወለጋ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ዓመት ከተማረ በኋላ ፣ በግብርና ሚኒስቴር ስር በሁመራ ከተማ በጊዜያዊነት ተመድቦ ይሠራ ነበር። ከተማዋ በኢዲዩ ስር ስትወድቅ በኅዳር ወር 1970 ተይዞ ሕዝብ በተሰበሰበበት ከሌሎች ሁለት ጓዶቹ ጋር ለመቀጣጫ በሚል እስከነሕይወቱ በጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ተቀበረ።መለሰ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበረ።