ማሬ በላይ ማሬ በላይ የተወለደው ጎንደር ጭልጋ ነው። በጎንደር ከተማ የፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነበር። ቀጥሎም በደባርቅ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት አገልግሏል። በ1970 ዓ/ም አጋማሽ ላይ የደርግ አባልና የአውራጃው አስተዳዳሪ በነበረው በገብረህይወት ትዕዛዝ እጅና እግሩን ታስሮ ከሌላ የመኢሶን ጓድ ጋር በሕይወት እያለ ሊማሊሞ ገደል ውስጥ ተወርውሮ ተገደለ።