ብርሃኑ (ለጊዜው የአባቱን ስም ማግኘት ያልተቻለ) ብርሃኑ፣ በ1970 ዓ.ም. አጋማሽ በጎንደር ክፍለ አገር የአውራጃ አስተዳዳሪ በነበረው ገብረሕይወት በተባለ የደርግ አባል ትዕዛዝ እጅና እግሩ ታስሮ ከነሕይወቱ ከሊማሊሞ ገደል ተወርውሮ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ።