አየለ ቁሜ

አየለ ቁሜ፣ ጎንደር፣ ማክሰኝት ከተማ ተወለደ። የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ማእረግ ያለፈ  ጎበዝ ተማሪ ነበር። በመቀጠልም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩነቨርሲቲ በሶሻል ሳይንስ ፋካልቲ የ2ኛ ዓመት ትምህርቱን ከአጠናቀቀ በኋላ የነጻ ትምህርት እድል አግኝቶ ግብጽ ሄደ። ከግብጽ እንደተመለሰ በጎንደር በአስተማሪነትና በጭልጋ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት አገለገለ።

መኢሶን የትግል ስልት ለውጥ ከአደረገ በኋላ ጥቅምት 4 ቀን 1970 ዓ/ም የደርግ አባልና የጎንደር ክፍለ አገር አስተዳዳሪ በነበረው በሻለቃ መላኩ ተፈራ ትእዛዝ ተይዞ ከፍተኛ ስቃይ ደረሰበት። ከዚያም  ደሙ ተቀድቶ ተገደለ። አስከሬኑም ከሌሎች አምስት የመኢሶን ጓዶች ጋር በሠአዘዞ ከተማ የጅምላ መቃበር ተጣለ።

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top