ጌትነት ዘውዴ
ጌትነት ዘውዴ፣ በ1937 ዓ.ም. አዲስ አበባ ተወለደ። የኮሌጅ ትምህርቱን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተከታትሎ በ1960 ዓም በፖለቲካ ሳይንስ የባቸለር ኦፍ አርትስ ዲገሪውን ተቀብሏል። ትምህርቱን እንደጨረሰ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጠረ።
በአብዮቱ ወቅት የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ ነበር። በመኢሶን አባልነቱ ምክንያት፣ ጥቅምት 29 ቀን 1969 ዓም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ አዲስ አበባ ከካዛንቺስ ከሥራ ወደቤቱ ሲመለስ፣ መንገድ ላይ በኢሕአፓ ነፍሰ ገዳይ ቡድን ተገደለ።
ጌትነት፣ ረጋ ያለ፣ ከመናገር ይልቅ ማዳመጥ የሚያዘወትር፣ በኮሌጅ ተማሪነቱ ዘመን በጓደኞቹ ዘንድ የተከበረ ሰው ነበር።