ደምቢ ዲሳሳ

ደምቢ ዲሳሳ በወለጋ ክፍለ አገር ጊምቢ አውራጃ ላሎ ጮሊ በሚባል ቀበሌ በ1941 ተወለደ። እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ጊምቢ ከተማ በሚገኘው የደጃዝማች ገ/እግዚአብሔር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታተለ:: በመቀጠልም አዲስ አበባ በሚገኘው የጄኔራል ዊንጌት አዳሪ ትምህርት ቤት በመግባት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በ1962 ዓ.ም አጠናቀቀ። ብዙዎች የትምህርት ቤት ጓደኞቹ በረጅም ርቀት የሩጫ ችሎታው ያስታውሱታል።  

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀም በጅባትና ሜጫ አውራጃ በጥቁር እንጭኒ ትምህርት ቤት ለሦስት ዓመታት በአስተማሪነት ካገለገለ በኋላ በ1965 የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ለመከታተል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  ዩኒቨርሲቲ ገባ። በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ለረዥም ጊዜ ተይዞ የቆየውን የአምስት እና የአሥር ሺህ ሜትር ሩጫ ሬኮርድ በማሻሻል በስሙ ለማስመዝገብ ችሎ ነበር። 

የኢትዮጵያ አብዩትን ተከትሎ የእድገት በህብረት ዘመቻ ሲታወጅ በዩኒቨርሲቲ ተማሪነቱ በጫንጮ ምድብ ጣቢያ ተመድቦ  ገበሬዎችን በማደራጀት እና የመሬት ዓዋጁን በሥራ ለመተርጎም የበኩሉን አስተዋጻኦ አድርጓል።  በመቀጠልም በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ካድሬ ሁኖ በተለያዩ ስፍራዎች አገልግሏል። 

በነሐሴ 1969 ዓ.ም መኢሶን የትግል ስልት ለውጥ ለማድረግ ሲገደድ ደምቢም ሙሎ ወረዳ  ከሄደው የመኢሶን ቡድን ጋር ሄደ። ነሐሴ 30 ቀን 1969 ዓ.ም. ደምቢ ይገኝበት የነበረው ቡድን ያለበት ስፍራ በደርግ የጸጥታ ሃይሎች ተደርሶበት ሲከበብ ዶ/ር ከበደ መንገሻ እና አቶ ዳንኤል ታደሰ እራሳቸውን ሲሰዉ፣ ደምቢ ዲሳሳ እና አብረውት የነበሩት ምትኩ ተርፋሳና ደምበል አየለ በከበባቸው ሃይል የመትረየስ እሩምታ ተከፍቶባቸው እየተታኮሱ ወደቁ። 

ደምቢ  ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የ28 ዓመት ወጣት  ነበር።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top