ኃይሉ ብርሃኑ ኃይሉ፣ ጎንደር ቆላ ድባ ተወለደ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አቋርጦ እዚያው ቆላ ድባ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት መሥራት ጀመረ። በደርግ አባል እና የከፍለ አገሩ አስተዳዳሪ በሻለቃ መላኩ ተፈራ ትእዛዝ ታስሮ ብዙ ስቃይ ደረሰበት። ከዚያም ጥቅምት 4 ቀን 1970 ዓ.ም. ደሙ ተቀድቶ ከተገደለ በኋላ ከሌሎች አምስት የመኢሶን ጓዶች ጋር በአዘዞ ከተማ ጅምላ መቃብር ተጣለ።